በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩጋንዳው ፕሬዘዳን ዮሪ ሞሴቬኒ ልጅ በቀጣዩ ምርጫ እንደማይወዳደር አስታወቀ 


ፋይል፡ የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ ሙሁኦዚ ካይኔሩጋባ
ፋይል፡ የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ ሙሁኦዚ ካይኔሩጋባ

በ2026 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እወዳደረዋለሁ ያለው የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ ሙሁኦዚ ካይኔሩጋባ ይህን ሃሳቡን መተውንና በምትኩ አባቱን እንደሚደግፍ አስታውቋል።

እአአ ከ1980 ጅምሮ ሃገሪቱን እየመሩ የሚገኙት የ80 አመቱ ፕሬዘዳንት ሞሰቬኒ በአሁኑ ወቅት የመከላከያ ሃይሉ መሪ ያደረጉት ልጃቸውን ሙሁኦዚ ካይኔሩጋባ ቀጣይ ተተኪያቸው ያደርጉታል ተብሎ በብዙዎች ተገምቷል፡፡

ካይኔሩጋባ ቀድሞ ትዊተር ይባል በነበረው የኤክስ ማህበራዊ ድህረ ገጽ ባስፈረው መልዕክት "በ2026 በድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ እንደማልኖር ማሳወቅ እፈልጋለሁ።" ሲል ተናግሯል።

ሙሴቬኒ ሰባተኛ የስልጣን ዘመን ይሹ እንደሆነ እስካሁን በግልፅ አልተናገሩም።

"ከፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ በኋላ ማንም ሲቪል ዩጋንዳ አይመራም።የፀጥታ ሀይሉ አይፈቅድም።ቀጣዩ መሪ ወታደር ወይም ፖሊስ ይሆናል"ሲል ካይሩጋባ አክሏል።

ካይኔሩጋባ በምርጫው ለመወዳደር ማሰቡን ቀደም ብሎ ባሰስታወቀበት ወቅት የኡጋንዳ ፖለቲካ ውስጥ አዲስ ደም የሚያስፈልግበት ጊዜ መሆኑንም ገልጾ ነበር፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG