በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ሁለት መምህራን መገደላቸውን የአካባቢው አስተዳደር አስታወቀ


 በኢትዮጵያ በአማራ ብሔራዊ ክልል የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ደብረ ማርቆስ
በኢትዮጵያ በአማራ ብሔራዊ ክልል የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ደብረ ማርቆስ
በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ሁለት መምህራን መገደላቸውን የአካባቢው አስተዳደር አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:52 0:00

“በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ፣ ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን ትናንት መስከረም 8/2017 ዓ.ም. በፋኖ ታጣቂዎች ተገድለዋል” ሲል የአካባቢው አስተዳደር አስታወቀ።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የስናን ወረዳ አስተዳዳሪ አየነው ደለለ፣ ሁለቱ መምህራን የተገደሉት በፋኖ ታጣቂዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ መሆኑን ገልጸዋል።

“ታጣቂዎቹ መምህራኑን የገደሉት፣ ትምህርት ለማስጀመር እንቅስቃሴ አድርጋችኋል በማለት ነው” ሲሉም አስተዳዳሪው ከሰዋል፡፡

ዋሽንግተን ለሚገኙ የአሜሪካ ድምጽ ባልደረቦች በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ የሰጡት የአማራ ፋኖ በጎጃም የውጭ ጉዳይና የዲያስፖራ ጉዳዮች መምርያ ሃላፊ እንደሆኑ የገለጡልን አቶ ስሜነህ ሙላቱ በበኩላቸው “ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት አድርገን በጦርነቱ ምክንያት ልጆቻችን እንዳይጎዱ በሚል ትምህርት መጀመር የለበትም ብሎ የወሰነውን ነው እያስፈጸምን ያለነው” ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ስሜነህ ሙላቱ አክለውም “በስናን ወረዳ ሙያቸው መምህራን በመሆኑ በፋኖ የተገደሉ የሉም“ ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ድምጽ ስለ ግድያውም ሆነ ግድያው በማን እንደተፈጸመ ከገለልተኛ ወገን አላረጋገጠም፡፡

በሌላ በኩል፣ በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን፣ በመንግስት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ግጭት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ዘንድሮም ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታውቋል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ አውጃ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር መሆናቸውንና ጉዳት ሊደርስብኝ ይችላል በማለት ስማቸውን በይፋ እንዳንጠቅስ የጠየቁን ግለሰብ “በአካባቢው ትምህርት ዘንድሮ አለመጀመሩ ለተማሪዎችም ሆነ ለመምህራን ትልቅ ኪሳራ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

“ለትምህርት አለመጀመር ዋነው ምክንያት ኃላፊነት የሚወስድ አካል አለመኖሩ ነው” ሲሉም አክለዋል፡፡

የምስራቅ ጎጃም የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት “የትምህርት ዘመኑ በተጀመረ አራት ቀናት ውስጥ ከ710 ሺ ተማሪዎች መካከል 42 ሺ ተማሪዎች ብቻ ናቸው ትምህርት የጀመሩት፡፡” ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG