በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንግረስ የተቋቋመው ግብረ ኃይል በትረምፕ የግድያ ሙከሪያ ዙሪያ ማብራሪያ ጠይቋል


የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ
የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ

ባለፈው ሐምሌ በቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ላይ የተፈፀመውን የግድያ ሙከራ በመመርመር ላይ ያለውና ከሁለቱ ፓርቲዎች የተውጣጣው የኮንግረስ የጋራ ግብረ ኃይል፣ ትላንት እሁድ ለሁለተኛ ጊዜ ፍሎሪዳ ላይ ተፈጽሟል የተባለውን የግድያ ሙከራ በተመለከተ ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑንና የፕሬዝደንቱ ልዩ ጥበቃ ቡድን (ሲክረት ሰርቪስ) ማብራሪያ እንዲሰጥ መጠየቁን አስታውቋል።

የቀድሞው ፕሬዝደንት ላይ ጉዳት ባለመድረሱ እፎይታ እንደተሰማቸውና፣ ማንኛውንም ዓይነት የፖለቲካ ሁከት ተቀባይነት እንደሌለው፣ የግብረ ኃይሉ መሪዎች የሆኑት የፍሎሪዳው የሪፐብሊካን ፓርቲው የም/ቤት ዓባል ማይክ ኬሊ እና የኮሎራዶው የዲሞክራቲክ ፓርቲው የም/ቤት ዓባል ጄሰን ክሮው አስታውቀዋል። ግብረ ኃይሉ ያሚያገኘውን አዳዲስ መረጃም ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ ተናግረዋል።

ዶናልድ ትረምፕ ትላንት እሁድ በባለቤትነት በያዙት የጎልፍ ክለብ በመጫወት ላይ ሳሉ፣ ራያን ወስሊ ራውት የተባለው ተጠርጣሪ በሽቦ አጥር በኩል ጠመንጃውን ሲያነጣጥር የተመለከቱ የሲክረት ሰርቪስ አባላት ተኩስ መክፈታቸው ታውቋል።

ራያን ወስሊ ራውት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሄደውን ጦርነት በመቃወም፣ ገንዘብ ለማሰባሰብና በጎ ፈቃደኞችን ለመመልመል ድህረ ገጽ አዘጋጅቶ ነበር። “ለዩክሬን ተዋግቼ እሞታለሁ” ሲልም በአንድ ወቅት በ X ማኅበራዊ መድረክ ላይ መልዕክቱን አስፍሮ ነበር። ከሁለት ዓመታት በፊት በኪቭ የነፃነት አደባባይ በሠልፍ ላይ ሳለ የአሶስዬትድ ፕረስ በቪዲዮ ቀርጾት እንደነበር የዜና ወኪሉ በዘገባው አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG