በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቱኒዚያ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ ቅስቀሳ ተጀመረ 


ቱኒዚያውያን በዋና ከተማቸው ቱኒዝ በፕሬዚዳንት ካይስ ሰኢድ ላይ ተቃውሞ ሲያሰሙ፣ መስከረም 3 2017 ዓ.ም.
ቱኒዚያውያን በዋና ከተማቸው ቱኒዝ በፕሬዚዳንት ካይስ ሰኢድ ላይ ተቃውሞ ሲያሰሙ፣ መስከረም 3 2017 ዓ.ም.

የቱኒዚያ የፕሬዝዳንታዊ የምርጫ ወቅት ቅስቀሳ ትላንት ቅዳሜ በይፋ ተጀምሯል፡፡ ይህም የሃገሪቱ ሁኔታ እያሸቆለቆለ ነው ያሉ ቱኒዚያውያን ቁጣቸውን በዋና ከተማው ጎዳናዎች ላይ በመውጣት ከገለጹ ማግስት ነው፡፡

በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ባለስልጣናት ለወራት የዘለቀ የእስር ማዕበል ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ትልቁ በሚመስለው ተቃውሞ፣ አርብ ዕለት በመቶዎች የሚቆጠሩ ቱኒዚያውያን ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ የ “ ፖሊስ መንግስት” ሲሉ የጠሩት ይህ ድርጊት እንዲያበቃ ጠይቀዋል፡፡

አንዳንዶቹ ሰልፈኞችም ለመንግስት "ሰብአዊ መብት አማራጭ አይደለም" የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ወጥተዋል፡፡ የተቃውሞ ሰልፉ ከሳምንት በፊት ያስጀመረው የሰሜን አፍሪካዋ ሃገር ትልቁ ተቃዋሚ ፓርቲ ኤናሃዳ ቀደም ሲል ባልታየ መጠን ከፍተኛ አባላቶቹ በጅምላ መታሰራቸውን አስታውቋል።

እስሩ የመጣው የአሁኑ የሃገሪቱ ፕሬዘዳንት ካይ ሰኢድ በመጭው ጥቅምት ወር በድጋሚ ለመመረጥ ቅስቀሳ ለማድረግ እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ነው፡፡

ፕሬዘዳንት ካይ ሰኢድ እ.ኤ.አ. በ2019 ወደ ስልጣን ሲመጡ የፀረ ሙስና ዘመቻዎችን እንደሚያደርጉ ተስፋዎችን ሰጥተው የነበሩ ቢሆንም ስልጣን ከያዙ በኋላ የሀገሪቱን ፓርላማ በማገድ እና ህገ መንግስቱን እንደገና በመፃፍ ስልጣናቸውን ለማጠናከር ብዙ ጥረት አድርገዋል በሚል ይነቀፋሉ ። በስልጣን ዘመናቸው፣ ጋዜጠኞችን፣ አነቃቂዎችን፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችን እና የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን በርዕዮተ ዓለም ልዩነት ምክንያት አስረዋል በሚል ትችቶች ይደርሱባቸዋል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG