በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፑቲንን ዛቻ አጣጣሉ


የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ላሚ ከዩናይትድ ስቴጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በኪየቭ ዩክሬን ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት፣ መስከረም 1 2017 ዓ.ም.
የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ላሚ ከዩናይትድ ስቴጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በኪየቭ ዩክሬን ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት፣ መስከረም 1 2017 ዓ.ም.

የብሪታንያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴቪድ ላሚ ዛሬ እሁድ በሰጡት አስትያየት ዩክሬን ከሩሲያ ምድር ዘልቆ ጉዳት የማድረስ አቅም ያለው የረዥም ርቀት መሳሪያ እንድትጠቀም መፍቀድ ኔቶን ከሞስኮ ጋር ከለየለት ጦርነት ውስጥ ያስገባታል በሚል የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለሰነዘሩት ማስጠንቀቂያ “በመደንፋት” ወንጅለዋቸዋል።

የዩናይትድ ስቴት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር በዋይት ሀውስ ተገናኝተው ኪየቭ ከምዕራቡ ዓለም የሚቀርብላትን የጦር መሳሪያ አጠቃቀም ላይ ህጎችን ለማቃለል በዚህ ሳምንት መወያየታቸውን በሩሲያ እና በምዕራቡ ዓለም መካከል ያለው ውጥረት ከፍ ስለማድረጉም ተገልጿል፡፡

"እኔ እንደማስበው ፑቲን የሚያደርጉት ነገር አቧራ ወደ አየር ማስነሳት ነው " ሲሉ ለቢቢሲ የተናገሩት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዴቪድ ላሚ "ብዙ ድንፋታ አለ። ስለ ታንኮች ያስፈራራል፣ ስለ ሚሳኤሎች ያስፈራራል፣ ስለ ኑክሌር ጦር መሳሪያ ያስፈራራል።" ሲሉም አክለዋል፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ሩሲያ ውስጥ በጥልቀት ኢላማዎችን ለመምታት የብሪታኒያ “ስቶርም ሻዶ” በመባል የሚታወቁት ሚሳኤሎችን እና በአሜሪካ የተሰሩ ኤቲ ኤሲ ኤም ኤስ የተሰኙ ሚሳኤሎችን ለመጠቀም ፍቃድ ሲጠይቁ ቆይተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG