በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የየመን አማፂያን ወደ እስራኤል የተኮሱት ሚሳኤል በአለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያው የማስጠንቀቂያ ድምፅ አስነሳ


ከየመን የተተኮሰው ሚሳኤል ማእከላዊ እስራኤል ከወደቀ በኋላ አንድ የፖሊስ መኮንን በተነሳው የእሳት አደጋ ዙሪያ ያለውን አካባቢ ሲፈተሽ ያሳያል፣ መስከረም 5 ቀን 2017 ዓ.ም. (AP Photo/Ohad Zwigenberg)
ከየመን የተተኮሰው ሚሳኤል ማእከላዊ እስራኤል ከወደቀ በኋላ አንድ የፖሊስ መኮንን በተነሳው የእሳት አደጋ ዙሪያ ያለውን አካባቢ ሲፈተሽ ያሳያል፣ መስከረም 5 ቀን 2017 ዓ.ም. (AP Photo/Ohad Zwigenberg)

በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማጽያን ዛሬ እሁድ የተኮሱት ሚሳኤል በማዕከላዊ እስራኤል በሚገኝ ክፍት መሬት ላይ ቢያርፍም በቤን ጉሪዮን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የማስጠንቀቂያ ድምጾች እንዲነሳ አድርጓል፡፡ ይህም ለአመት በተጠጋው የጋዛ ጦርነት የደረሰ የቅርቡ ጥቃት ነው ፡፡

እስራኤልም ለዚህ ጥቃት ወታደራዊ ምላሽ እንደምትሰጥ ፍንጭ ሰጥታለች።እስካሁን በሰው ህይወት ላይም ሆነ ሌላ ያደረሰው ከፍተኛ ጉዳት ስለመኖሩ የተገለጸ ነገር ባይኖርም የእስራኤል መገናኛ ብዙሀን ሰዎች ወደ ቤን ጉሪዮን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለመጠለል ሲሽቀዳደሙ የሚያሳይ ምስል አሳይተዋል።

የአውሮፕላን ማረፊያው ባለስልጣናት በበኩላቸው አውሮፕላን ማረፊያው ብዙም ሳይቆይ መደበኛ ስራውን መጀመሩን ገልጸዋል።

በማዕከላዊ እስራኤል ገጠራማ አካባቢ የእሳት ቃጠሎ የታየ ሲሆን የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በማዕከላዊ ሞዲን ከተማ በባቡር ጣቢያ ውስጥ በሰዎች መወጣጫ ላይ ያረፈ የጸረ ሚሳኤል ቁርጥራጭ ምስሎችን አሳይተዋል።

የእስራኤል ጦር ባለ ብዙ አየር መከላከያው ሚሳኤሉን ከአየር ላይ ለማስቀረት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ቢያደርግም እስካሁን የተሳካለት ስለመሆኑ አልታወቀም ብሏል። ክስተቱ አሁንም እየተገመገመ መሆኑን የገለጸው ጦሩ ሚሳኤሉ በአየር ላይ የተበጣጠሰ ይመስላልም ሲል ገልጿል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከጥቃቱ በኋላ በካቢኔ ስብሰባ ላይ በሰጡት አስተያየት ተመሳሳይ ምላሽ እንደሚሰጥ ፍንጭ ሰጥተዋል።

“ሁቲዎች እኛን ለመጉዳት ለሚያደረጉት ማንኛውም ሙከራ ከባድ ዋጋ የሚከፍሉ መሆናችውን ማወቅ ነበረባቸው።” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የሁቲ አማፂያኑ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ያህያ ሳሬ በቴል አቪቭ አካባቢ “ወታደራዊ ኢላማ” ላይ ያነጣጠረ የባላስቲክ ሚሳኤል መተኮሳቸውን ተናግረዋል።

አማጽያኑ በእስራኤል እና በፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ መካከል በጋዛ ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሚሳኤሎችን በተደጋጋሚ ወደ እስራኤል ተኩሰዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG