በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእስራኤል ጦር የተተኮሰባት አሜሪካዊት ቀሳቅሽ ተቀበረች


የአሜሪካ እና ቱርክ ጥምር ዜግነት ያላት ማኅበራዊ ቀስቃሽ አይሴኑር ኢዝጊ ኢይጊ የቀብር ስነ ስርዓት በቱርክ
የአሜሪካ እና ቱርክ ጥምር ዜግነት ያላት ማኅበራዊ ቀስቃሽ አይሴኑር ኢዝጊ ኢይጊ የቀብር ስነ ስርዓት በቱርክ

በእስራኤል ወታደር የተገደለችው ቱርክ-አሜሪካዊት ማኅበራዊ ቀስቃሽ ወዳጅ እና ቤተሰቦች በቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉበት በዛሬው ዕለት፤ እስራኤል በማዕከላዊ እና ደቡባዊ ጋዛ በፈጸመችው የአየር ድብደባ ጥቃት በትንሹ 14 ሰዎች ሞቱ።

በጋዛ ከተማ በደረሰው የአየር ድብደባ ሦስት ሴቶች እና አራት ህጻናትን ጨምሮ 11 ሰዎች ያሉበት አንድ መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት የደረሰ ሲሆን፤ ሌላኛው ጥቃት ደግሞ በካኻን ዩኒስ በጦርነት የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን መጠለያን ላይ መፈጸሙን የጋዛ ሲቪል መከላከያ ዛሬ ቅዳሜ አስታውቋል።

የሲያትል ከተማ ነዋሪ የሆነበረችው፣ የ26 ዓመቷ፤ የአሜሪካ እና ቱርክ ጥምር ዜግነት ያላት ማኅበራዊ ቀስቃሽ አይሴኑር ኢዝጊ ኢይጊ በትውልድ መንደሯ ቱርክ ዲዲም በኤጂያን ባህር አካባቢ ተቀብራለች።

የእስራኤል ጦር ኢይጊ በጎርጎርሳዊያኑ መስከረም ስድስት የተገደለችው፤ በዌስት ባንክ በእስራኤል ሃይሎች “በተዘዋዋሪ እና ባለማወቅ” በጥይት ተመትታ ሊሆን ይችላል ሲል አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ጥቃቱን የተመለከቱ እስራኤላዊ ተቃዋሚዋ የተተኮሰባት የእስራኤል ሰፋሪዎችን ተቃውሞ ከተደረገው ስለፍ በኋላ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የቱርክ ፓርላማ አፈ-ጉባኤ ኑማን ኩርቱሉስ “የልጃችንን ደም መሬት ላይ ፈሶ አይቀርም፤ ለዚህ ግድያ ሃላፊነት እና ተጠያቂነት እንዲኖር እንጠይቃለን” ሲሉ ለሀዘንተኞች ተናግረዋል።

በተያያዘ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ዩናይትድ ስቴትስ፣ ግብፅ እና ኳታር የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና በሐማስ የተያዙትን የቀሩትን እስረኞች እንዲፈቱ ግፊት እያደረጉ ባለኡበት በአሁን ሰዓት የማኅበራዊ ቀስቃሿን ሞት አውግዘዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG