በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ እና ዩክሬን 206 እስረኞችን ተቀያየሩ


የዩክሬን ወታደሮች መስከረም 04/2016 ዓ.ም
የዩክሬን ወታደሮች መስከረም 04/2016 ዓ.ም

በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ሸምጋይነት የተካሄደውን ድርድር ተከትሎ፤ ሩሲያ እና ዩክሬን ለሁለት ቀናት ባደረጉት ከፍተኛ የእስረኞች ልውውጥ እስከ ዛሬ ቅዳሜ ድረስ 206 እስረኞችን ተለዋውጠዋል ስትል አረብ ኤመሬት አስታወቀች።

ፕሬዘዳንት ቮልደሚየር ዘለንስኪ 82 ወታደሮች እና 21 የጦር ኃላፊዎችን ጨምሮ 103 ዩክሬናዊያን ተመልሰዋል ያሉ ብለዋል።

በሌላ በኩል የሩሲያ መከላከያ ደግሞ 103 ሩሲያዊያን ወታደሮች በነሐሴ ወር ዩክሬኖች ድንገተኛ ጥቃት በፈጸሙባት ከርስክ ድንበር ላይ መለዋወጣቸውን አስታውቋል።

ዘለንስኪ በቴሌግራም የመልዕክት መላላኪያ ላይ “በተሳካ ሁኔታ ተጨማሪ 103 ተዋጊዎችን ከሩሲያ ይዞታ አስለቅቀን ወደ ዩክሬን አምጥተናል” ብለዋል።

የእስረኞች ልውውጡ በተባበሩት አረብ ኤመረቶች መመራቱን ዋም የተሰኘ የሀገሪቱ ጣቢያ ዘግቧል። የአውሮፓዊያኑ 2024 ከጀመረበት አንስቶ የተባበሩት አረብ ኤመሬቶች ያካሄደችው ስምንተኛ ድርድር መሆኑ ተገልጿል።

ኪዬቭ እና ሞስኮ ሩሲያ እ.ኤ.አ በየካቲት 2022 ካደረገችው ሙሉ ወረራ ጀምሮ ቁጥራቸው የበዙ እስረኞችን የተቀያየሩ ሲሆን ይሄ የአሁኑ ሦስተኛቸው ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG