በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜን ጎንደር፣ ዳባት ከተማ አንድ ታጣቂ 2 ሰዎችን ገደለ


Ethiopia Map
Ethiopia Map
በሰሜን ጎንደር፣ ዳባት ከተማ አንድ ታጣቂ 2 ሰዎችን ገደለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:57 0:00

በሰሜን ጎንደር ዞን፣ ዳባት ከተማ አንድ ታጣቂ ባለፈው አርብ ፈፀመው በተባለ ጥቃት፣ አንድ ኤርትራዊ ስደተኛን ጨምሮ፣ 2 ሰዎች መገደላቸውን፣ ስደተኞች ተናገሩ፡፡ በዛው ሳምንት፣ በዳባት ወረዳ፣ በአለምዋጭ መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ 2 ኤርትራውያን ስደተኞችም ታጣቂዎች ባደረሱባቸው ጥቃት ቆስለው ወደ ጎንደር ሆስፒታል መወሰዳቸውን፣ ስደተኞቹ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል፡፡

የመጠለያ ጣቢያው የሚገኝበት የዳባት ወረዳ፣ ጭላ ቀበሌ አስተዳደር በበኩሉ፣ በዳባት ከተማ ሁለት ሰዎች በታጣቂ መገደላቸውን አረጋግጧል፡፡ በአብዛኛው ኤርትራውያን ስደተኞች የሚኖሩበት የአለምዋጭ መጠለያ ጣቢያን የፀጥታ ኹኔታ ለማሻሻልም እየሰራን ነው ብሏል፡፡

በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG