በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኔታንያሁ ከሀማስ ጋር ጦርነቱን እንደሚቀጥል ቃል ገቡ


ጋዛ ጳጉሜ 01/2016 ዓ.ም
ጋዛ ጳጉሜ 01/2016 ዓ.ም

12ኛ ወሩን የጀመረው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት፤ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጋዛ ከሚገኙት የሀማስ ታጣቂዎች ጋር ጦርነቱን ለመቀጠል እሁድ ዕለት ቃል ገብተዋል። ኔታኒያሁ ሀገራቸው “በኢራን የክፋት ምህዋር በሚመራ ገዳይ አስተሳሰብ የተከበበች ናት” መሆኗን በምክንያት አስቀምጠዋል።

በዌስት ባንክ እና በዮርዳኖስ መካከል በሚገኘው አለንባይ ድልድይ መሻገሪያ፤ ሥስት እስራኤላውያንን የገደለው የታጣቂዎች ጥቃት የእስራኤል የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ በመመለስ አጥቂውን ገድለዋል። ኔታንያሁ፣ በሳምንታዊው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ስብሰባ ላይ፣ የቅርብ ጊዜውን የመካከለኛው ምስራቅ ብጥብጥ አውግዘዋል።

በሌላ በኩል በጋዛ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት ሁለት ሴቶች፣ ሁለት ህጻናት እና አንድ የሲቪል መከላከያ ከፍተኛ ባለስልጣን ጨምሮ አምስት ሰዎችን ሞተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG