በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አልጄሪያ ፕሬዝዳንቷን እየመረጠች ነው


አልጄሪያውን ድምጽ እየሰጡ ነው
አልጄሪያውን ድምጽ እየሰጡ ነው

አልጄሪያውያን ለ20 ዓመታት የገዙትን የቀድሞውን ፕሬዝዳንት በአመጽ ከስልጣን እንዲወርዱ ካደረጉ አምስት ዓመታት በኋላ አዲስ ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ዛሬ ቅዳሜ ድምጽ እየሰጡ ነው፡፡
በዴሞክራሲ ኃይሎች የተቀሰቀሰው የሠራዊቱ ክፍል የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ከሥልጣን ካስወገደ በኋላ በሚደረገው ምርጫ ሶስት ተፎካካሪዎች ቀርበዋል፡፡ ለሠራዊቱ ቅርበት አላቸው የተባሉት የወቅቱ ፕሬዝዳንት አብዱልመጂድ ታቡን ያሸንፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሁለቱ ተፎካካሪዎች ከእስላማዊ ፓርቲ አብደላሂ ሀሳኒ ቸሪፍ እና ከሶሻሊስት ሃይሎች ዮሰፍ አዉሺሽ ናቸው፡፡
ብዙ ዜጎች በምርጫው ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል ሲናገሩ አንዳንዶችም ምርጫውን በመቃወም ጥርጣሬያቸውን ከወዲሁ እያሰሙ መሆኑ ተነግሯል፡፡
የተሳትፎ መቀዛቀዝ ታይቶበታል በተባለው በዚህ ምርጫ ትልቁ መነጋገሪያ ማን ያሸንፋል ሳይሆን ምን ያህል ሰው ወደ ምርጫው ጣቢያ ሳይሄድ ቤቱ ተቀምጧል የሚል ነው ሲል አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
አልጄሪያውያን በከፍተኛ የኑሮ ውድነት እና በድርቅ ምክንያት በተፈጠረው የውሃ እጥረት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ዘገባው አመልክቷል፡፡
እኤአ በ2019 ብዙ የመራጮች ተሳትፎ ሳይታበት በተካሄደው ምርጫ የተመረጡት ታቡን የሥልጣናቸውን ተገቢነት ለማሳየት በዚህኛው ምርጫ የተሳትፎ ቁጥር ከፍ እንዲል የሚፈልጉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG