በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያው የእሳት ቃጠሎ ሁኔታቸው ያልታወቀ ተማሪ ልጆቻቸውን ወላጆች በጭንቅ እየተጠባበቁ ነው


ወላጆችና እና የማህበረሰቡ አባላት እኤአ መስከረም 6/2024 የእሳት ቃጠሎው አደጋ በደረሰበት ስፍራ ተሰባስበዋል፡
ወላጆችና እና የማህበረሰቡ አባላት እኤአ መስከረም 6/2024 የእሳት ቃጠሎው አደጋ በደረሰበት ስፍራ ተሰባስበዋል፡

ኬንያ ውስጥ ከትላንት በስቲያ ሀሙስ በአንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት 17 አዳጊ ወጣቶች በሞቱበት የእሳት አደጋ እስካሁን አድራሻቸው ያልታወቁ ተማሪ ልጆቻቸውን ወላጆች በጭንቅ እየተጠባበቁ ነው፡፡

የኬንያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋቻጓ አደጋው በተከሰተበት ቦታ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እስካሁን 70 የሚደርሱት አዳጊ ወጣቶች ሁኔታ አለመታወቁን ተናግረዋል።

የተማሪዎቹ ቤተሰቦች እስከ ዛሬ ቅዳሜ ድረስ የልጆቻቸውን ሁኔታ ለማወቅ በጭንቅ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

በቃጠሎው የቆሰሉ 14 ህጻናት በሆስፒታል ህክምና እየተሰጣቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፖሊስ የአንዳንዶቹን ተጎጂዎች ማንነት ለመለየት ምርመራ በማድረግ ላይ መሆኑን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

ቃጠሎው በተነሳበት በማዕከላዊ ኬንያ ኔየሪ አውራጃ እንደራሻ አካዳሚ የማደሪያ ክፍል ውስጥ ከ150 በላይ ወንዶች ተኝተው እንደነበር ተነግሯል፡፡

የቃጠሎው መንስኤ እስካሁን በውል ባይታወቅም በቅድሚያ የወጡ ዘገባዎች በመኝታ ክፍል ውስጥ መጨናነቅ እና የደህንነት መርህ ጥሰቶች እንደነበሩ ጠቁመዋል።

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሀዘን አውጀው ስለ አደጋው ሙሉ ምርመራ እንደሚደረግና ተጠያቂነት እንደሚኖር ቃል ገብተዋል፡፡

800 ህጻናት ተማሪዎችን የሚያስተናግደው ትምህርት ቤት ከናይሮቢ በስተሰሜን 170 ኪሎሜትሮች ላይ ይገኛል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG