ግብፅ ለምክር ቤቱ በጻፈችው ደብዳቤ “ሕልውናዬን እና የሕዝቦቼን ጥቅም ለማስከበር ሁሉንም እርምጃዎች ለመውሰድ ዝግጁ ነኝ” ብላለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የግድቡ ሁለት ተርባይኖች ከሳምንት በፊት ኃይል ማመንጨት መጀመራቸውን እና የግድቡ ግንባታም መገባደዱን መግለጻቸውን ተከትሎ ግብፅ ባሰማችው ቅሬታ፣ የኢትዮጵያ 'የአንድ ወገን እርምጃ' የቀጠናውን መረጋጋት አደጋ ላይ ይጥላል ብላለች፡፡
ይህንን አስመልክቶ ሞያዊ ትንታኔ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው የቀጣናዊ እና አካባቢያዊ መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር የሺጥላ ወንድሜነህ፣ ግብፅ ደብዳቤ የጻፈችው “ቀጣይ እወስዳለሁ ያለቻቸውን እርምጃዎች ህጋዊ መልክ ለማስያዝ እና ጫናዋን ከፍ ለማድረግ ያለመ ነው” ይላሉ፡፡
መድረክ / ፎረም