በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቻይና-አፍሪካ መድረክ ላይ ለመሳተፍ መሪዎች ቤጂንግ በመግባት ላይ ናቸው


የቻይና ዳንሰኞች የሞዛምቢኩን ፕሬዝዳንት ፊሊፔ ኒዩሲ በቤጂንግ ካፒታል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ሲያደርጉ፣ ነሐሴ 27 2016 ዓ.ም. (Wang Zhao/Pool Photo via AP)
የቻይና ዳንሰኞች የሞዛምቢኩን ፕሬዝዳንት ፊሊፔ ኒዩሲ በቤጂንግ ካፒታል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ሲያደርጉ፣ ነሐሴ 27 2016 ዓ.ም. (Wang Zhao/Pool Photo via AP)

በተፈጥሮ ሃብት ከታደለችው አፍሪካ ጋራ ግንኙነቷን ማጠናከር የምትሻው ቻይና፣ በቤጂንግ በሚደረገው የቻይና-አፍሪካ መድረክ ላይ የሚሳተፉ የአህጉሪቱ መሪዎችን ቀይ ምንጣፍ ዘርግታ በመቀበል ላይ ነች፡፡

ለአህጉሪቱ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር የመሠረተ ልማትና ሌሎችም ፕሮጀክቶች ብድር የምትሰጠው ቻይና፣ ከኮቪድ ወረርሽኝ ወዲህ የምታስተናግደው ከፍተኛው የዲፕሎማሲ መድረክ እንደሆነ አስታውቃለች፡፡ ከአንድ ደርዘን በላይ የሚሆኑ መሪዎችና ተወካዮች በመድረኩ ይሳተፋሉ ተብሏል።

ቻይና በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሰራተኞቿን ወደ አፍሪካ በመላክ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እንዲገነቡ በማድረግ ላይ ስትሆን፣ በምትኩ ደግሞ በአህጉሪቱ በብዛት ከሚገኘው ወርቅ፣ መዳብ፣ ሊቲዩም እና ሌሎችም በሌላ ሥፍራ የማይገኙ ማዕድናትን ትወስዳለች፡፡

በከፍተኛ መጠን የምታቀርበው ብድር ለመሠረተ ልማት ግንባታ ቢውልም፣ አህጉሪቱን ከፍተኛ ዕዳ ውስጥ እየጨመረ ነው የሚል ትችትም አስከትሏል።

በዓለም ኢኮኖሚዋ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቻይና፣ ለአፍሪካ ትልቁ የንግድ ሸሪክ ስትሆን፣ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት አጋማሽ ብቻ 167.8 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ እንደተከናወነ የቻይና መንግስት ብዙሃን መገናኛ አስታውቋል።

በዚሁ መድረክ ላይ ለመገኘት ቤጂንግ የገቡት የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ከፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ጋራ እንደተወያዩ የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ዛሬ በ X ማኅበራዊ መድረክ ላይ አስታውቀዋል።

ሁለቱ ወገኖች በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ እንደተወያዩም ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ላይ አስፍረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG