በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ - ሶማሊያ ውዝግብ እና የአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ


የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ዓርብ ነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ኢትዮጵያ አዲስ በሚቋቋመው የሶማሊያ የሰላም ተልዕኮ ውስጥ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል፡፡ አዲሱ የሶማሊያ የሰላም ተልዕኮ ለኢትዮጵያ የደኅንነት ስጋት ምንጭ መኾን የለበትም ብለዋል፡፡

በአንጻሩ ከሁለት ሳምንት በፊት ከግብፅ ጋር የመከላከያ ስምምነት የተፈራረመችው ሶማሊያ: በበኩሏ አዲስ በሚቋቋመው ተልዕኮ ውስጥ የሚሳተፉትን ሀገራት መምረጥ እንደምትፈልግ ገልጻ ጎረቤቷ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችውን አወዛጋቢ የመግባቢያ ስምምነት ውድቅ ካላደረገች ከዚህ አዲስ ከሚቋቋመው ተልዕኮ እንድትገለል አደርጋለሁ ስትል ዝታለች፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:18:50 0:00

ዓለም አቀፍ እውቅና ያልተሰጣት የራስ ገዟ ሶማሊላንድ በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ፣ ደግሞ “የግብፅ ጦር በሶማሊያ መገኘቱን አጥብቄ አወግዛለኹ” ብላለች።

በዚህ ጉዳይ ላይ የአፍሪካ ቀንድ እና መካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ከፍተኛ የጥናት ባለሙያ የሆኑትን ዶክተር በለጠ በላቸው እና የሞቃዲሾው ተንታኝ ፕሮፌሰር አፍያሬ ኢሊሚ ያነጋገርንበትን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG