የቀድሞው ኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ የተገደሉበት የሄሊኮፕተር አደጋ በዋነኛነት የተከሰተው ከባድ ጭጋግ በታከለበት (አስቸጋሪ) የአየር ሁኔታ ምክንያት መሆኑን ፣ የመጨረሻ ምርመራ ውጤቶችን ዋቢ ያደረገው የኢራን መንግስት ቴሌቭዥን በዛሬው እለት ዘግቧል።
የሀገሪቱ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኔ ተተኪ ሊሆኑ ይችላሉ በሚል ሲታዩ የከረሙት ወግ አጥባቂው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ፣ በግንቦት ወር በአዘርባጃን ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ ተራራማ አካባቢ ነበር ሄሊኮፕተራቸው ተከስክሶ ህይወታቸው ያለፈው።
የኢራን መንግስት ቴሌቭዥን እንደዘገበው "የሄሊኮፕተሩ መከስከስ ዋናው ምክንያት በአካባቢው ያለው የአየር ሁኔታ አስቸጋሪ መሆኑ ነው " ሲል የመጨረሻው ምርመራ ውጤት መደምደሙን አስታውቋል።
ድቅድቅ ጭጋግ ራኢሲ እና ባልደረቦቻቸውን ይዛ የነበረችው ሄሊኮፕተር ከተራራ እንድትላተም ምክንያት መሆኑን ጉዳዩ ያጣራ ዘንድ በኢራን ጦር የተሾመው ከፍተኛ ኮሚቴ ያወጣው ዘገባ አመልክቷል።
የኢራን ጦር ቀድሞ ባዋጠው ሪፖርት ላይ ከአደጋው ጋር በተገናኘ የስህተትም ሆነ የጥቃት ማሳያ ማስረጃዎች በምርመራው ወቅት እንዳልተገኙ አስታውቆ ነበር (ሮይተርስ) ።
መድረክ / ፎረም