በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤላዊ - አሜሪካዊው ኸርሽ ጎልድበርግ-ፖሊን ጨምሮ እስራኤል በጋዛ ውስጥ የ6 ታጋቾችን አስከሬን ማግኘቷ ተገለፀ።


.
.

እስራኤል የ6 ታጋቾችን አስክሬን ጋዛ ውስጥ ማግኘቷን በዛሬው ዕለት አስታወቀች። ከእነዚህ መካከል በሀማስ ከተያዙ እና በእጅጉ ታዋቂ ከነበሩት መካከል አንዱ የነበረው ወጣቱ እስራኤላዊ-አሜሪካዊ ኸርሽ ጎልድበርግ- ፖሊን ይገኝበታል ።ከዓለም መሪዎች ጋር የተገናኙት ወላጆቹ ነጻ እንዲወጣ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል ።

የእስራኤል ጦር በስፍራው ከመድረሱ ጥቂት ቀደም ብሎ ስድስቱም ታጋቾች መገደላቸውን አስታውቋል። የታጋቾቹ አስክሬን መገኘት ፣ ብዙ እስራኤላውያን ለ10 ወራት የዘለቀውን ጦርነት ለማቆም ከሃማስ ጋር በሚደረግ ስምምነት ታጋቾችን በህይወት መመለስ ባለመቻላቸው ተጠያቂ ባደረጓቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ላይ ህዝባዊ ተቃውሞ እንዲካሄድ የሚጠይቁ ጥሪዎችን ቀስቀሷል ።ድርድሩ ካለ አንዳች ስምምነት ለወራት መጓተቱ ይታወሳል ።


ኔትንያሁ " ርህራሄ በጎደለው መንገድ " ታጋቾቹን ገድሏል ያሉት ሀማስን ሀገራቸው ተጠያቂ እንደምታደርግ ተናግረዋል። " ታጋቾችን የገደለ ስምምነትን አይሻም " ያሉት ኔትንያሁ ፣ታጣቂውን ቡድን ድርድሩን በማደናቀፍም ከሰዋል ።

ታጣቂዎቹ የ23 ዓመቱን ኸርሽ ጎልድበርግ-ፖሊን እና አራት አጋቾችን ያፈኗቸው ጥቅምት 7 ሀማስ በደቡብ እስራኤል እየተከናወነ በነበረ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ጥቃት በከፈተበት ወቅት ሲሆን ፣ ይህ ክስተት የጦርነቱ መነሾ ሆኗል ።

ከበርክሌይ፣ ካሊፎርኒያ የመጣው ኸርሽ ፣ በፈንጂ ጥቃት ምክንያት ግራ አጇን አጥቷል። በሚያዚያ ወር ላይ ሀማስ ባሰራጨው ቪዲዮ ላይ ኸርሽ በህይወት መኖሩ እና ግራ እጁን እንዳጣ የታየ ሲሆን ፣ በምላሹ መንግስት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ የበለጠ እንዲሰራ የሚያሳስብ አዲስ ተቃውሞ በእስራኤል አስነስቷል።

የእስራኤል ጦር በተጨማሪም ፣ከሙዚቃ ዝግጅቱ ላይ የታፈኑት ፣ የ25 ዓመቱ ኦሪ ዳንኢኖ ፣ የ24 ዓመቷ ኤደን የሩሻለሚ ፣ የ27 ዓመቱ አልሞግ ሳሩሲ እና የ33 ዓመቱ አሌክሳንደር ላቦኖቭ ከሟቾች መካከል መሆናቸውን አስታውቋል ። ስድስተኛዋ ሟች የ40 ዓመቷ ካርሜል ጋት ቤሪ ከሚባለው አረሶ አደር ማህበረሰብ የታገተች እንደነበር ተገልጿል ።

አስክሬኖቹ የተገኙት በደቡብ ጋዛ በምትገኘው ራፋ ውስጥ ካለ ዋሻ መሆኑን ጦር አስታውቋል ። ዋሻው ከሳምንት በፊት ካይድ ፋርሃን አልካዲ የተሰኙ የ52 ዓመት ታጋች በሕይወት ከተረፉበት ስፍራ አንድ ኪሎሜትር ርቆ እንደሚገኝ ተነግሯል ።

የወታደራዊው ቃል አቀባይ ሌተናል ኮሎኔል ናዳቭ ሾሻኒ እንዳሉት ሰራዊቱ በአካባቢው ታጋቾች እንዳሉ በወቅቱ ቢያምንም ነገር ግን የተለየ መረጃ እንዳልበረው ገልጸዋል ።ታጋቾችን ሀማስ እንደገደላቸው ጥርጣሬ እንደሌላቸው ተናግረዋል ።


ሀማስ ታጋቾችችን ለመልቀቅ እና በምላሹም ጦርነቱ እንዲቆም ፣ የእስራኤል ኃይሎች እንዲወጡ እና ቁልፍ ሚና ያላቸው ተዋጊዎችን ጨምሮ ከፍተኛ ብዛት ያላቸው ፍልስጤማዊያን እስረኞች እንዲለቀቁ መጠየቁ ይታወሳል ።

አይዛት አል ሪሽቅ የተባሉት የሐማስ ከፍተኛ ባለስልጣን ፣ሀማስ በሐምሌ ወር እንደተስማማበት የገለጸው እና በአሜሪካ የተደገፈውን የተኩስ አቁም ሀሳብ እስራኤል ብትቀበል ኖሮ ታጋቾቹ በህይወት ይተርፉ እንደነበር ተናግረዋል። የታጋቾቹ ቤተሰቦች ሀገሪቱ ውስጥ የሚደረግ እንቅስቃሴ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል ።

ኔታንያሁ ሀማስ እስኪጠፋ ድረስ ጦርነቱን እንደሚቀጥል ገልፀው ታጋቾቹን ወደ ቤት ለማምጣት ወታደራዊ ግፊት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል (AP)።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG