በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጠለምት ወረዳ 10 ሰዎች በመሬት ናዳ መሞታቸውን አስተዳደሩ አስታወቀ


በጠለምት ወረዳ 10 ሰዎች በመሬት ናዳ መሞታቸውን አስተዳደሩ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:19 0:00

በሰሜን ጎንደር ዞን በጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ እና ቅዳሜ በጣለው ከባድ ዝናም የተነሣ በተከሠተው የመሬት ናዳ፣ 10 ሰዎች መሞታቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

የዞኑ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰላም ይኹን ሙላት ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ከሞት አደጋው በተጨማሪ ከሁለት ሺሕ በላይ ሰዎች ከአካባቢያቸው መፈናቀላቸውን እንዲሁም በቤት እንስሳት እና በሰብል ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል፡፡

የጠለምት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጋሻው እንግዳው፣ እስከ አሁን የአራት ሰዎች አስከሬን መገኘቱን ጠቅሰው፣ የስድስት ሰዎች አስከሬን ግን እየተፈለገ መኾኑን ተናግረዋል፡፡ የመሬት ናዳ ስጋት ያለባቸው ሌሎች ቀበሌዎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የሚቲዎሮሎጂ ትንበያ እና ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዲሬክተር ዶክተር አሳምነው ተሾመ፣ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ “በአገሪቱ በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ ከመደበኛ በላይ መጠን ያለው ዝናም የሚጠበቅ ይኾናል፤” ብለዋል፤ ቀጣዮቹ ሁለት ወራትም ከባድ እንደሚኾኑ አሳስበዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG