በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል እና ሂዝቦላ ከባድ የተኩስ ልውውጥ አደረጉ


ከፍተኛ የተኩስ ልውውጡ ለረጅም ጊዜ የተፈራውን ጦርነት የቀሰቀሰ ባይመስልም፣ ነባሩ ውጥረት ​​ግን ቀጥሏል ።
ከፍተኛ የተኩስ ልውውጡ ለረጅም ጊዜ የተፈራውን ጦርነት የቀሰቀሰ ባይመስልም፣ ነባሩ ውጥረት ​​ግን ቀጥሏል ።

እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ ዛሬ ረፋድ ላይ የአየር ድብደባ ያደረሰች ሲሆን ፣ ጥቃቱ በሂዝቦላህ ላይ የተፈጸመ የቅድመ መከላከል ጥቃት መሆኑን አስታውቃለች ። ታጣቂ ቡድኑ ባለፈው ወር ከዋና አዛዦቹ የአንዱን ግድያ ለመበቀል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን እና ድሮኖችን ማስወንጨፉን ገልጿል።

ከፍተኛ የተኩስ ልውውጡ ለረጅም ጊዜ የተፈራውን ጦርነት የቀሰቀሰ ባይመስልም፣ ነባሩ ውጥረት ግን ቀጥሏል ። ይህ በንዲህ እንዳለ ግብፅ ለ10 ወራት ጋዛ ውስጥ የዘለቀው የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት በተኩስ አቁም ስምምነት እንዲቋጭ ለማድረግ ያለመ የከፍተኛ አመራሮች ውይይቶችን እያስተናገደች ትገኛለች። ዲፕሎማቶች ድርድሩ የቀጠናውን ውጥረት ይቀርፋል የሚል ዕምነት አላቸው።

የእስራኤል ጦር ጥቃቱን ያደረሰው ሂዝቦላህ በእስራኤል ላይ ከባድ የሮኬቶች እና ሚሳኤሎችን ለማስወንጨፍ በማቀዱ ነው ብሏል። ብዙም ሳይቆይ ሄዝቦላህ ባለፈው ወር ከመስራቾች መካከል የሆነውን ፉአድ ሽኩርን ለገደለው ፣ እስራኤል በቤሩት ላደረሰችው የአየር ጥቃት የመጀመሪያ ምላሽ የዑሚሆን ጥቃት በወታደራዊ ይዞታዎች መፈጸሙን አስታውቋል።

ረፋድ ላይ፣ የተኩስ ልውውጡ ያበቃ መስሏል ። ሁለቱም ወገኖች ጥቃቶቻቸው ያነጣጠሩት በወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ብቻ እንደነበረ ተናግረዋል ። በሊባኖስ በተፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 3 ሰዎች ተገድለዋል፣ በእስራኤል በኩል የደረሰ ጉዳት እስካሁን አልተገለጸም ።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የካቢኔ ስብሰባ ባተጀመረበት ሰዓት እንደተናገሩት ወታደራዊ ኃይሉ በሰሜን እስራኤል ላይ ያነጣጠሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ማምከኑን ገልጸው ዜጎቹ ከሀገሪቱ ጦር ግንባር ዕዝ የሚሰጠውን መመሪያ እንዲከተሉ አሳስበዋል።

ጥቃቱ እስራኤል ውስጥ ባሉ በርካታ ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ያነጣጠሩ ከ320 በላይ የካትዩሻ ሮኬቶች እና “ብዙ ቁጥር ያላቸው” ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ያካተተ መሆኑን የገለጸው ሂዝቦላ በበኩሉ ፣ የመጀመሪያው ምዕራፍ የአጸፋ ጥቃት ማብቃቱን አስታውቋል ። የአሁኑ ጥቃት ወደ እስራኤል ግዛት ይበልጡኑ የዘለቁ ጥቃቶችን ለመፈጸም እንደሚያችለውም ተናግሯል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG