በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሃማስ ልዑክ ስለተኩስ አቁም ለመነጋገር ወደ ካይሮ አምርቷል


ካሊል አልኻያ የሃማስ ከፍተኛ ባለሥልጣን
ካሊል አልኻያ የሃማስ ከፍተኛ ባለሥልጣን

በከፍተኛ የሃማስ ባለስልጣን ካሊል አልኻያ የሚመራው የሃማስ ልዑክ በሰሞኑ የተኩስ አቁም ንግግር ዙሪያ ከሸምጋዮች የቀረበውን ለመስማት ዛሬ ቅዳሜ ወደ ካይሮ አቅንቷል ሲል የፍልስጤማውያኑ ቡድን ባወጣው መግለጫ አመለከተ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ እና የእስራኤል ልዑካን ከትላንት በስቲያ ሐሙስ እና ትላንት አርብ በተኩስ አቁሙ ስምምነት ዙሪያ ልዩነቶችን በመፍታት ላይ ያተኮሩ ስብሰባዎችን በካይሮ እንዳካሄዱ ሁለት የግብጽ የደህንነት ምንጮች እንደነገሩት ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የሃማስ ከፍተኛ ባለስልጣን ኢዛት አል-ሪሽቅ “የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እኤአ ሀምሌ 2 ያቀረቡትን ሀሳብ መቀበሉንና ተግባራዊ እንደሚያደርገውም በገባው ቃል መሰረት” ለመፈጸም ቁርጠኛ መሆኑን ዛሬ ቅዳሜ ተናግረዋል፡፡

ባላፈው ሀምሌ ሃማስ የጋዛ ጦርነትን ለማስቆም ከተደረሰው ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነውን ከ16 ቀናት በኋላ ወታደሮችን እና ወንዶችን ጨምሮ የእስራኤል ታጋቾችን በመልቀቅ ንግግር ለመጀመር መስማማቱን የሃማስ ከፍተኛ ባላሥልጣን ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡

ሌላው የሃማስ ባለስልጣን ማህሙድ ማርዳዊ፣ “የልዑካን ቡድኑ አሁን ወደ ካይሮ አቀና ማለት ሃማስ በሚቀጥለው ዙር በቀጥታ ይሳተፋል ማለት እንዳልሆነ” ለሃማስ ቅርበት ላለው የመገናኛ ብዙሃን መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ግብፅ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ካታር በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲኖር፣ ታጋቾችን እና ፍልስጤማውያን እስረኞች እንዲለቀቁ ለወራት ሲቋረጥና ሲቀጥል የቆየውን ሽምግልና ሲያካሂዱ ቆይተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG