በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሸቀጦች የዋጋ ተመን “ውጤት አላመጣም” የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች


የሸቀጦች የዋጋ ተመን “ውጤት አላመጣም” የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:34 0:00

የሸቀጦች የዋጋ ተመን “ውጤት አላመጣም” የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች

የሶማሌ ክልል፣ በጂጂጋ ከተማ በተመረጡ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ተመን ማውጣቱ፣ “የሚፈለገውን ውጤት አላመጣም” ሲሉ፣ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ግን፣ የዋጋ ተመኑ፥ “አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሬን ለመቆጣጠር አስችሎኛል፤” ብሏል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ፣ በምግብ እና በግንባታ ግብአቶች ላይ የተጋነነ የዋጋ ጭማሬ ተስተውሎ እንደነበር ያስታወቀው የጂጂጋ ከተማ ንግድ እና ትራንስፖርት ቢሮ፣ ለእነኚኽ የተመረጡ ምርቶች የዋጋ ተመን በመቀመጡ ዋጋውን ለማረጋጋት መቻሉን ገልጿል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የኢኮኖሚ ባለሞያ፣ “በተመረጠ ኹኔታ ይህን መሰል ርምጃ መውሰድ፣ የነጻ ገበያ መርሕን የሚጥስ አይደለም” ሲሉ ርምጃውን ደግፈዋል።

በድሬዳዋም በአንዳንድ ምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ቅናሽ መታየቱን ጨምሮ ከድሬዳዋ የተጠናቀረው ዘገባ ተጨማሪ አለው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG