በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
“ባልታወቁ ታጣቂዎች የተያዘችውን የሰገን ከተማ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መልሰው ተቆጣጥረዋል” የሰገን ዙሪያ ወረዳ

“ባልታወቁ ታጣቂዎች የተያዘችውን የሰገን ከተማ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መልሰው ተቆጣጥረዋል” የሰገን ዙሪያ ወረዳ


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ኮንሶ ዞን፣ ሰገን ዙሪያ ወረዳ፣ ሰገን ከተማ፣ ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ አንስቶ በተፈጸመ ጥቃት “የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ስምንት የማኅበረሰብ ፖሊስ አባላትን ጨምሮ 14 ደርሷል” ሲል የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል ።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ኡርማሌ ኡጋንዴ፥ "የፀረ ሰላም ኀይል እና ጽንፈኞች" ሲሉ በጠሯቸው ታጣቂዎች ለአምስት ቀናት፣ በታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር የቆየችውን የሰገን ከተማ፣ ዛሬ የመንግስት ኃይሎች መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል።

አስተዳዳሪው፣ ታጣቂዎቹ፥ "ከአጎራባቹ የጋርዱላ ዞን ዲራሼ ወረዳ ሀይበና ቀበሌ የመጡ ናቸው ሲሉ የጋርዱላ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ኩናሎ ግን፣ "ጥቃት አድራሾቹ፥ ከዲራሼ ወረዳ አስተዳደር ጋራ አይገናኙም፤ በዞኑ መንግሥት የሚደገፉ ናቸው መባሉም ሐሰት ነው፤" ሲሉ ክሱን አስተባብለዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የሰገን ከተማ ነዋሪዎች፣ ጥቃቱን ሸሽተው፣ ወደ ዞኑ ዋና ከተማ ካራት እና በአቅራቢያው ወደሚገኙ ቀበሌዎች መሸሻቸውን ጠቁመዋል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG