በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ የሽብር ጥቃቶችን ጨምሮ ‘ብርቱ ተደራራቢ አደጋዎች ተደቅነውባታል’ ሲሉ የጸጥታ ባለ ሥልጣናት አስታወቁ


የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ክሪስቶፈር ራይ በብሩክሊን ሴንተር ሚኒሶታ ውስጥ በቃለ መጠይቅ ወቅት ለጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ፣ ነሐሴ 15 2016 ዓ.ም.
የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ክሪስቶፈር ራይ በብሩክሊን ሴንተር ሚኒሶታ ውስጥ በቃለ መጠይቅ ወቅት ለጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ፣ ነሐሴ 15 2016 ዓ.ም.

የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ አስከባሪ ተቋማት የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል እየጣሩ ባሉበት በአሁኑ ወቅት፣ አገራቸው ከየማዕዘናቱ ከፍተኛ የአደጋ ስጋት እንደገጠማት የፌድራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ተናገሩ።

"በሥራ ዓለም ተሰማርተው በቆየሁበት ዘመን ሁሉ እንዲህ እንዳሁኑ ያለ የተለያዩ አደጋዎች በአንድ ጊዜ ስጋት የደቀኑበትን ጊዜ መለስ ብዬ እንዳስብ ተገድጃለሁ” ሲሉ የኤፍቢአይ ዲሬክተር ክርስቶፈር ሬይ አገራቸው ተደቅኖባታል ያሉትን ሁኔታ አብራርተዋል።

ሬይ ይህን አስተያየት የሰጡት በተለያዩ የጸጥታ ተቋማት መሃከል ባሉት የትብብር ግንኙነቶች ዙሪያ ለመናገር በትላንትናው ዕለት በምንያፖሊሱ የድርጅታቸው የመስክ ጽ/ቤት በተገኙበት እና ከአሶሺዬትድ ፕሬስ የዜና ወኪል ጋር ቃለ ምልልስ ባደረጉት ወቅት ነው።

የድሬክተሩ የማስጠንቀቂያ ቃል የተሰማው ኤፍቢአይ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ሽብርተኝነትን፣ ቻይና የምትፈጽማቸውን የስለላ ድርጊቶች፣ እንዲሁም የአእምሮ ንብረት ስርቆት እና በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ የውጭ ጣልቃ ገብነት የደቀኗቸውን ከፍተኛ ስጋቶች ለመመከት ጥረት በያዘበት ወቅት ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG