በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን እንዳያስገቡ አገደች


 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ

በኢትዮጵያ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎችን እንዳያስገቡ እግድ ተጣለ፡፡

እነዚኽ አካላት በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ብቻ እንዲያስገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጻፈላቸው ደብዳቤ አሳስቧል፡፡

ርምጃው፣ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔ አካል እንደኾነ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢዩ ተድላ ተናግረዋል፡፡

የምጣኔ ሀብት ባለሞያው አቶ ክቡር ገና፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ብቻ እንዲገቡ የተላለፈው ውሳኔ፣ የነዳጅ ወጪን ከመቀነስ አንጻር አስተዋፅኦ ቢኖረውም፣ ለዘርፉ የሚያስፈልጉ መሠረተ ልማቶች ያሉበት ኹኔታ አብሮ መታሰብ እንዳለበት ይመክራሉ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:25 0:00

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG