በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ በረራዎችን አስተጓጎለ


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከለሊቱ 09፡00 ሰአት ጀምሮ በነበረው ከፍተኛ ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት አብዛኞቹ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ የነበሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሊያርፉ ባለመቻላቸው በአቅራቢያ ወደሚገኙ አማራጭ ኤርፖርቶች ተመልሰው እንዲያርፉ መገደዳቸውን አስታወቀ፡፡

ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም-አቀፍ የጠዋት በረራዎቻቹ ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን ያመለከተው አየር መንገዱ በተሳፋሪዎቹ ላይ የጉዞ ዕቅዶች ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ መስተጓጉሎችን ለመቅረፍ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG