በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዲሞክራቲክ ፓርቲው ብሔራዊ ጉባኤ ሶስተኛ ምሽት በመካሄድ ላይ ነው


የቀድሞ ፕሬዝደንት ቢል ክሊንተን
የቀድሞ ፕሬዝደንት ቢል ክሊንተን

ዛሬ ለሶስተኛ ምሽት በመቀጠል ላይ ባለው የዲሞክራቲክ ፓርቲው ብሔራዊ ጉባኤ ላይ፣ ፓርቲውን በመወከል በምክትል ፕሬዝደንትትነት የሚወዳደሩትን ቲም ዋልዝ እንዲሁም የቀድሞ ፕሬዝደንት ቢል ክሊንተን ንግግር እንደሚያደርጉ በመጠበቅ ላይ ነው።

መድረኩ ቲም ዋልዝ ዛሬ ምሽት ራሳቸውን ከአሜሪካ ሕዝብ ጋራ የሚያስተዋውቁበት ይሆናል ተብሏል። የፓርቲውን የምርጫ ዘመቻ እንዲሁም የምሽቱን ዋና መልዕክት እንደሚያስተላልፉም ይጠበቃል።

የሶስተኛ ምሽቱ አብይ መፈክርም “ለነፃነት የሚደረግ ትግል” እንደሆነ የጉባኤው አስተናጋጆች አስታውቀዋል።

ምሽቱን ደመቅ ለማድረግም በጉባኤ ንግግር ችሎታቸው የሚታወቁት የቀድሞ ፕሬዝደንት ቢል ክሊንተን እንዲሁም የቀድሞ የተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፐሎሲ ይገኙበታል። ሌሎችም በርካታ የፓርቲው ከፍተኛ ዓባላት ንግግር ያደርጋሉ። አንዳንዶቹ ዓባላት ቀደሞ ብለው ንግግራቸው አሰምተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG