ከአሜሪካ አውራ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ዴሞክራቲክ ፓርቲ፣ ብሔራዊ ጉባዔውን በቺካጎ ከተማ በሰኞ ዕለት ጀምሯል። ይህ ጉባዔ ፓርቲው ህዳር ላይ በሚደረገው የሀገሪቱ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ላይ ዕጩ ተወዳዳሪ የሚያደርገውን አመራሩን ይፋ የሚያደርግበት፣ ተቀባይነትን ያስገኙልኛል ያላቸውን ፖለቲካዊ መርሀ ግብሮች እና ስልቶች የሚያስተዋውቅበት፣ እንዲሁም የመራጮችን ድጋፍ በይፋ የሚጠይቅበት ግዙፍ መድረክ ነው።
ስለጉባዔው የመጀመሪያ ቀናት ክንውኖች እና ተያያዥ ጉዳዮች፣ ቺካጎ ከሚገኘው ባልደረባችን ሀብታሙ ስዩም ጋር የተደረገውን አጭር ቆይታ ይመልከቱ።
መድረክ / ፎረም