ከአንድ ዓመት በፊት በባሕር ዳር ከተማ በሕፃን ሄቨን አወት ላይ የተፈጸመው አሠቃቂ የመድፈርና የግድያ ድርጊት እንዲሁም ተያያዥ የህግ ጉዳዮች፣ ብዙዎችን ማስቆጣታቸውን ቀጥለዋል፡፡
የሕፃን ሄቨን እናት፣ ልጇን በአሠቃቂ ኹኔታ ካጣችበት ጊዜ አንሥቶ መጽናናት ተስኗት እንደቆየች፣ የቤተሰቧ አባል ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩ ሲሆን በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡን ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ብርሃኑ በጋሻው፣ የቅጣት ውሳኔው፣ ከድርጊቱ አንጻር በቂ እና አስተማሪ እንዳልኾነ አብራርተዋል፡፡
ማኅበረሰቡ በተለያዩ አማራጮች ቁጣውን መግለጹንና ድርጊቱን ማውገዙን ቀጥሏል፡፡
መድረክ / ፎረም