በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በፓርቲያቸው ጉባኤ ደማቅ አቀባበል ተደረላቸው


 ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

በትላንቱ የዲሞክራቲክ ፓርቲያቸው ጉባኤ እጅግ ላቅ ያለ አክብሮት የተቸረ ንግግር ያሰሙት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ የዳግም ምርጫ ዘመቻቸውን አቋርጠው በምትካቸው ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሀሪስ እንዲወዳደሩ ያደረጉበት ውሳኔ ትኩስ የመነቃቃት ስሜት ፈጥሯል። ባይደን ዳግም ለመመረጥ ይዘውት የነበረውን ዘመቻ ገትተው ቦታውን ለሃሪስ እንዲለቁ በርካታ የፓርቲያቸው አመራሮች ግፊት ካደረጉባቸው ሳምንታት በኋላ ትላንትናት ምሽት ወደ ጉባኤው መድረክ ብቅ ሲሉ ከፓርቲያቸው አባላት ‘የጀግና አቀባበል’ ነው የጠበቃቸው።

የቺካጎው ጉባኤ የመክፈቻ ምሽት የሥልጣን ዘመናቸውን በማጠናቀቅ ላይ ካሉት ፕሬዝዳንት ለመጭው አራት ዓመታት በእርሳቸው እግር እንዲተኩ ለተመኟቸው ምክትል ፕሬዝዳንታቸው ቦታውን ማስተላለፍ በመሰለ ስሜት ታስቦ የተሰናዳ ተደርጎም ታይቷል።

በጥልቅ ስሜት እንደተዋጡ ወደ መድረኩ ብቅ ያሉት ባይደን ከአራት ደቂቃዎች በላይ የዘለቀ ጭብጨባ እና የአክብሮት አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በሺዎች የሚገመቱት የጉባኤው ታዳሚዎች "ጆ እናመሰግናለን" ሲሉም በሆታ ለባይደን ምስጋናቸውን ሲገልጹ ተስተውለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG