በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ራሳቸውን የሚያጠፉ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ወጣቶች ቁጥር ለምን ጨመረ?


ራሳቸውን የሚያጠፉ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ወጣቶች ቁጥር ለምን ጨመረ?
please wait

No media source currently available

0:00 0:18:59 0:00

ራሳቸውን የሚያጠፉ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ወጣቶች ቁጥር ለምን ጨመረ?

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በየ11 ደቂቃው አንድ ሰው ራሱን እንደሚያጠፋ የአሜሪካ በሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ መስሪያቤት መረጃ ያሳያል። ባለፈው ዓመት ብቻ ወደ 50 ሺህ የሚጠጉ አሜሪካውያን ራሳቸውን አጥፍተዋል። በተለይ እድሜያቸው ከ10 እስከ 24 ዓመት ባሉ ወጣቶች ዘንድ ደግሞ 62 በመቶ የጨመረ ሲሆን፣ በዛ እድሜ ክልል ለሚገኙ ወጣቶች ዋና የሞት መንስዔም መሆኑንም ተመልክቷል።

ይህ ቁጥር ትውልደ ኢትዮጵያዊ ወይም ኢትዮጵያዊ-አሜሪካውያንን ወጣቶችም ያጠቃልላል። ቁጥሩ በጥናት ባይረጋገጥም፣ ራሳቸውን የሚያጠፉ ኢትዮጵያዊ አሜሪካውያን ወጣቶች ቁጥር እየጨምረ መሄዱን ባለሙያዎች ይናገራሉ። ለዚህ ምክንያቱ ምንድነው? ችግሩን እንዴት መፍታት ይቻላል? በሚለው ላይ ለመወያየት ስመኝሽ የቆየ በአሜሪካ የመድሃኒት ቁጥጥር አስተዳደር መስሪያ ቤት ውስጥ በፔዲያትሪክ ፋርማኮሎጂስትነት የምታገለግለውን ዶክተር ሊሊ ሙሉጌታ እና የማህበረሰብ ጥናት ባለሙያ እና በአፍሪካ ዲያስፖራ ማህበረሰብ ኮሌጅ ተደራሽነት ዙሪያ የሚሰራ ተቋም መስራች ማቲዮስ መስፍንን ስቱዲዮ ጋብዛ አነጋግራለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG