በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ የቬትናም ፕሬዘዳንት በቻይና ጉብኝት እያደረጉ ነው 


ፋይል፡ የቬትናም ፕሬዘዳንት ቱ ላም
ፋይል፡ የቬትናም ፕሬዘዳንት ቱ ላም

በቅርቡ ወደ ስልጣን የመጡት የቬትናም ፕሬዘዳንት ቱ ላም የመጀመርያ የጉብኝት መዳረሻቸው ቻይናን አድረገዋል፡፡

ይህም ምንም እንኳን የደቡብ እስያዋ ሃገር ቬትናም ከአሜሪካና ሌሎች ሃገራት ጋር ያላትን ወዳጅነት እያሳደገች ቢሆንም ከጎረቤት ሃገሯ ቻይና ጋር ያላትን ግኑኝነት ቅድሚያ እንደምትሰጠው አመላካች ተደርጎ ተወስዷል፡፡

ፕሬዘዳንቱ በሆንግ ኮንግ አቅራቢያ የምትገኘው ዋና የማምረቻ እና የወጭ ምርት ማዕከል በሆነችው ጓንግዙ ግዛትን መጎብኘታቸውን የቻይና መንግስት ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል።

በሶስት ቀናት የጉብኝት ፕሮግራማቸውም ከቻይናው ፕሬዘዳንት ሺ ጂፒንግ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩም ተመላክቷል፡፡

ይህ ጉብኝታቸው ላም የሀገሪቱ ከፍተኛ የፖለቲካ ቦታ የሆነውን የቬትናም ኮሚኒስት ፓርቲ ዋና ፀሀፊ መሆናቸው ከታወቀ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የተደረገ ነው።

ከ13 ዓመታት መሪነት በኋላ ባለፈው ወር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ንጉየን ፉ ትሮንግን በመተካት ነው ስልጣኑን መያዝ የቻሉት፡፡

ላም ከግንቦት ወር ጀምሮም በሃገሪቱ በአብዛኛው የክብር ማዕረግ ያለውን የሀገሪቱን ፕሬዝደንትነት ቦታን ይዘው ቆይተዋል።

አዲሱ መሪ ከቻይና፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሩሲያ እና ሌሎች ጋር ያለውን ግንኙነት የማመጣጠን የቀደሙ መሪዎች ስትራቴጂን እንደሚያስቀጥሉም ይጠበቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG