በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን በኩርስክ ድልድይ ለማፍረስ የምዕራባውያንን ሮኬቶች ተጠቅማለች - ሩሲያ


በሩሲያ ኩርስክ ግዛት የተመታው ድልድይ እኤአ ነሐሴ 16 ቀን 2024 ከተለቀቀው የማህበራዊ ሚዲያ ቪዲዮ የተወሰደው ። (የዩክሬን አየር ሃይል/ሮይተርስ)
በሩሲያ ኩርስክ ግዛት የተመታው ድልድይ እኤአ ነሐሴ 16 ቀን 2024 ከተለቀቀው የማህበራዊ ሚዲያ ቪዲዮ የተወሰደው ። (የዩክሬን አየር ሃይል/ሮይተርስ)


ዩክሬን በኩርስክ ግዛት የሚገኘውን ድልድይ ለማፍረስ የምዕራባውያንን ሮኬት ማስወንጨፊያ ተጠቅማለች ስትል ሩሲያ ከሰሰች፡፡

የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዩክሬን በኩርስክ ክልል በሴም ወንዝ ላይ ያለውን ድልድይ ለማፍረስ የምዕራባውያን ሮኬቶችም ምናልባትም አሜሪካ ሰራሹን ዘመናዊ ሮኬት (HIMARS) ተጠቅማለች ብሏል፡፡

ዩክሬን ሮኬቶችን ተጠቅማ ከአካባባዊ ሰላማዊ ዜጎችን ለማውጣት ሲረዱ የነበሩ በጎ ፈቃደኞችን ገድላለች ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ከሷል፡፡
በጥቃቱ ምን ያህል በጎ ፈቃደኞች እንደተገደሉ የተገለጸ መረጃ የለም።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ እንደገለፁት የኩርስክ ክልል በምዕራባውያን ሰራሽ የሮኬት ማስወንጨፊያዎች ሲመታ ይህ የመጀመሪያው ነው ብለዋል።

የዩክሬን ጦር አዛዥ ኦሌክሳንደር ሲርስኪ የኪየቭ ሃይሎች ወደ ምእራብ ሩሲያ ግዛት ዘልቀው በመግባት ወረራ ከጀመሩ ከ11 ቀናት በኋላ በኩርስክ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ከ 1 እስከ 3 ኪሎሜትር የሚሆኑ አካባቢዎችን መቆጣጠራቸውን ተናግረዋል፡፡

ኪቭ እኤአ ከነሀሴ 6 ጀምሮ በኩርስክ ክልል 1,150 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ውስጥ 82 ቦታዎችን መቆጣጠሯን አስታውቃለች።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በኩርስክ ግዛት በርካታ የዩክሬን ጥቃቶችን ማመከኑን ዛሬ ቅዳሜ ቢገልጽም አንዳችም ይዞታ ስለመቆጣጠሩ አልገለጸም፡፡

ምዕራባውያን ዩክሬን በሩሲያ ግዛት ላይ የምታደርገውን የመጀመሪያ የምድር ላይ ጥቃት በመደገፍ ያበረታታሉ ያለችው ሩሲያ፣ የኪቭ “የሽብር ወረራ” የጦርነቱን አቅጣጫ እንደማይለውጥ ገልጻለች።

የሩሲያ መሪ ቭላድሚር ፑቲን ጦርነቱን እኤአ በየካቲት 2022 የጀመሩትን ጦርነት እንዲያሸነፉ እንደማትፈቅድ የገለጸችው ዋሽንግተን የዩክሬንን አስደናቂ ወርራ የጦር መሳሪያ ድጋፏን ተገቢነት የሚያረጋግጥ የመከላከያ እምርጃ አድርጋ ወስዳዋለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG