እስራኤል ጋዛ ውስጥ ተፈናቃይ ፍልስጤማውያ በሚገኙበት ትምህር ቤት ላይ ባካሄደችው ጥቃት 90 ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ ሲቪሎች ተሟጋች ዛሬ ቅዳሜ አስታወቀ፡፡
የዛሬው ጥቃት የተፈፀመው በጋዛ ዳራጅ እየተባለ በሚታወቀው አካባቢ ሲሆን የእስራኤል ጦር እምርጃው በአል-ታቢን ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኘውን የሃማስ ማዘዣ ማእከል ኢላማ ያደረገ ነው ብሏል።
የጋዛ መንግስት የሚዲያ ፅህፈት ቤት ትምህርት ቤቱ ውስጥ ወደ 250 የሚጠጉ ሰዎችን መጠለላቸውን ገልጾ፣ ግማሾቹ ሴቶች እና ህጻናት ናቸው ብሏል።
ጋዛ ውስጥ በተከታታይ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ጨምሯል፣ እኤአ ከሀምሌ 6 ጀምሮ ቢያንስ 14 ትምህርት ቤቶች ተመትተው ከ280 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የጋዛ ባለስልጣናት ዘገባዎች ያመለክታሉ ሲል ኤኤፍፒ ዘስግቧል፡፡
ኤኤፍፒ ቴሌቪዥን ከስፍራው በቀጥታ ሲያሳያቸው የነበሩ ምስሎች በጥቃቱ ከውስጥና ከውጭ የወደመውን የትልቁን ግቢ ህንጻዎች ፍርስራሽ አሳይተዋል፡፡ በከፊል የወደመ የሚመስለውን የመስጅድ ህንጻ ጨምሮ ደም የፈሰሰባቸውን ወለሎችና ከፍርስራሾቹ የሚወጣውን ጭስ አሳይቷል፡፡
እስራኤል ጦር ስፍራው በአልታቢን ትምህር ቤት ውስጥ የተሰገሰገ የሀማስ ማዛዣና መቆጣጠሪያ መምሪያ ነበር ብሏል፡፡
መድረክ / ፎረም