በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመዳሰስ - መስማት እና ማየት የተሳናቸውን ያግባባል የተባለ ዐዲስ ቋንቋ ይፋ ኾነ


ፎቶ ፋይል፦ አስመራ፤ ኤርትራ
ፎቶ ፋይል፦ አስመራ፤ ኤርትራ

በመዳሰስ - መስማትም ኾነ ማየት የተሳናቸውን ሰዎች ሊያግባባ ይችላል፤ የተባለ ዐዲስ የመግባቢያ ቋንቋ፣ በሦስት ወጣት ኤርትራውያን የሥነ ልቡና ባለሞያዎች ተዘጋጅቶ፣ ባለፈው ሰኔ ወር መጨረሻ ይፋ ኾኗል፡፡

በኤርትራ የወጣቶች እና ተማሪዎች ማኅበር ጽሕፈት ቤት አዳራሽ በተከናወነ ዐዲሱን የመዳሰስ ቋንቋ የማስተዋወቂያ መርሐ ግብር ላይ ማብራሪያ የሰጡት ባለሞያዎቹ፣ በእጅ መዳፍ ላይ የተዘጋጁ ዘጠኝ ነጥቦችን ተጠቅሞ የፊደል ቅርጽ በመጻፍ መስማትም ኾነ ማየት የተሳናቸውን ሰዎች ለማግባባት የሚረዳ እንደኾነ አስረድተዋል፡፡

 በመዳሰስ - መስማት እና ማየት የተሳናቸውን ያግባባል የተባለ ዐዲስ ቋንቋ ይፋ ኾነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:58 0:00

ዐዲሱ የመግባቢያ ቋንቋ ኣድጎ እና ሰፍቶ በተገቢው መንገድ ተደራሽ መኾን ከቻለም፣ ከ40ሺሕ በላይ መስማት የተሳናቸውንና 20ሺሕ ማየት የተሳናቸውን የአገሪቱን ዜጎች ከማግባባት ባለፈ፣ ኹሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚያገናኝ አገራዊ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ ለመኾን እንደሚችል ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡ ለዚኽም ተግባራዊነት፣ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኘው የአስመራው ዘጋቢያችን ብርሃነ በርሀ፣ ወጣት የፈጠራ ባለሞያዎቹንና ተጠቃሚዎቹን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኳል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG