በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሃሪስ የእጩ ምክትል ፕሬዚዳንት ምርጫ ላይ የባለሞያዎች አስተያየት


ዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ፣ የሚኔሶታ አገረ ገዢ ቲም ዎልዝ በፊላደልፊያ በተካሄደው የምርጫ ዘመቻ ላይ፣ ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም.
ዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ፣ የሚኔሶታ አገረ ገዢ ቲም ዎልዝ በፊላደልፊያ በተካሄደው የምርጫ ዘመቻ ላይ፣ ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም.

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ፣ የሚኔሶታ አገረ ገዢ ቲም ዎልዝን እጩ ምክትል ፕሬዚዳንታቸው እንዲኾኑ መርጠዋቸዋል።

የአሜሪካ ድምፅም፣ ነዋሪነታቸው በዋሽንግተን ዙሪያ የኾነ የዴሞክራቲክ እና የሪፐብሊካን ፓርቲዎች ደጋፊዎችን በዚኹ ጉዳይ ላይ አነጋግሯል፡፡

የተመዘገቡ ዴሞክራት የኾኑት የሕግ ባለሞያው አቶ ዳንኤል ውብሸት፣ ቲም ዎልዝ በምርጫው ወሳኝ ድምፅ ከሚገኝበት ማዕከላዊ-ምዕራብ(ሚድ ዌስት) አካባቢ የመጡ መኾናቸውን ጠቅሰው፣ “ዲሞክራቶች የአካባቢውን ድምፅ እንዲያገኙ ዕድልን የሚፈጥር ነው፤” ብለዋል፡፡

በአንጻሩ የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊ እንደኾኑ የሚናገሩት አቶ ላባን ሥዩም በበኩላቸው፣ እነዚኽ አካባቢዎች ቀድሞውንም ዲሞክራቶችን የሚመርጡ እንደኾኑ አውስተው፣ “በምርጫው ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ የለም፤” ይላሉ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ይከታተሉ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:52 0:00

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG