የባንግላዴሽ ኤታማዦር ሹም የኖቤል ተሸላሚውን ሙሃማድ ዩኑስ የሃገሪቱ ጊዜያዊ መንግስት መሪ ሆነው መመረጣቸውንና ነገ ሐሙስ ምሽት ላይ ከፓሪስ እንደተመለሱ ቃለ መሃላ እንደሚፈጽሙ አስታውቀዋል።
ኤታማዦር ሹሙ ጀኔራል ዌከር ዛማን፣ ሙሃማድ ዩኑስን በመሪነት የሾሙት የ300 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ተቃውሞ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን ሼክ ሃሲና ሃገር ለቀው እንዲወጡ ማስገደዱን ተከትሎ ነው።
ተቃውሞው የተነሳው መንግስት ሥራን በኮታ ለመሥጠት በመወሰኑ እንዲሁም ሼክ ሃሲና ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ የቆዩ፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚጠየቁና ምርጫ ያጭበረበሩ ናቸው በሚል ነበር።
በቅርቡ በተፈጸመው ሁከት ተሳታፊ የሆኑ ተጠያቂ እንደሚሆኑ የኤታማዦር ሹሙ ጀኔራል ዌከር አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት ለወጉ ያህል አገሪቱን የሚመሩት ፕሬዝደንት ሞሃመድ ሻሁቡዲን ትላንት ማክሰኞ ፓርላማውን በትነዋል።
ሙሃማድ ዩኑስ ባንክ በመመስረት በአነስተኛ ብድር ድህነት እንዲቀንስ አድርገዋል በሚል ከ18 ዓመታት በፊት የኖቤል የሰላም ተሸላሚ ሆነዋል።
መድረክ / ፎረም