በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ የምርጫ ዘመቻው ተጧጡፏል

የዲሞክራቲክ ፓርቲው ፕሬዝደንታዊ እጩ የሆኑት ካመላ ሄሪስ እና እጩ ምክትል ፕሬዝደንት በመሆን አብረዋቸው የሚወዳደሩት የሜኒሶታ አገረ ገዥ ቲም ዋልዝ በፔንሲልቬኒያ የምርጫ ዘመቻ ላይ፣ ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. (AP Photo/Matt Rourke)
የዲሞክራቲክ ፓርቲው ፕሬዝደንታዊ እጩ የሆኑት ካመላ ሄሪስ እና እጩ ምክትል ፕሬዝደንት በመሆን አብረዋቸው የሚወዳደሩት የሜኒሶታ አገረ ገዥ ቲም ዋልዝ በፔንሲልቬኒያ የምርጫ ዘመቻ ላይ፣ ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. (AP Photo/Matt Rourke)

በአሜሪካ ምርጫ የሁለቱ ፓርቲዎች እጩዎች በመጪዎቹ ቀናት ምርጫውን ለማሸነፍ ወሳኝ በሆኑ ግዛቶች ላይ ዘመቻ ያደርጋሉ።

በትላንትናው ዕለት የዲሞክራቲክ ፓርቲው ፕሬዝደንታዊ እጩ የሆኑት ካመላ ሄሪስ፣ እጩ ምክትል ፕሬዝደንት በመሆን አብረዋቸው የሚወዳደሩት የሜኒሶታ አገረ ገዥ ቲም ዋልዝ መሆናቸውን ፔንሲልቬኒያ ላይ በተደረገ የምርጫ ዘመቻ ላይ አስተዋውቀዋል።

የዲሞክራቲክ ፓርቲው እጩዎች ከዛሬ ጀምሮ ምርጫውን ይወስናሉ በሚባሉት ግዛቶች ውስከንስን፣ ሚቺጋን፣ አሪዞና፣ እና ኔቫዳ ዘመቻ ያደርጋሉ።

የሪፐብሊካን ፓርቲው ምክትል ፕሬዝደንታዊ እጩው ጄ ዲ ቫንስ በተመሳሳይ በውስከንስን እና ሚቺጋን ዘመቻ ያደርጋሉ። በሰሜን ካራሎይና በሳምንቱ መጨረሻ ሊያደርጉ ያቀዱት ዘመቻ ወደ አካባቢው እየመጣ ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ወደ ሌል ጊዜ ተላልፏል።

የ60 ዓመቱ ቲም ዋልዝ በሚኒሶታ አገረ ገዢነታቸው በተከተሏቸው ፖሊሲዎች ምክንያት በተራማጅ አሜሪካውያን ዘንድ ተቀባይነት እንደሚያገኙ በመነገር ላይ ነው።

የቀድሞ የአሜሪካ ብሔራዊ ዘብ አባልና የቀድሞ መምህር መሆናቸውም በገጠር ያሉ ነጭ ድምጽ ሰጪዎችን ድጋፍ ያስገኝላቸዋል ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG