በምዕራብ ጎንደር ዞን ከመጠለያ ወጥተው መኖሪያቸውን በመንገድ ዳር ባደረጉት የሱዳን ስደተኞች ላይ፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ በተፈጸመ ጥቃት አራት ሰዎች መቁሰላቸውን፣ የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር በምሕጻሩ ዩኤንኤችሲአር ለአሜሪካ ድምፅ ገለጸ፡፡
በጥቃቱ ማዘኑን የገለጸው ተቋሙ፣ የቆሰሉት አራቱ ሰዎች፣ በጎንደር ሆስፒታል የሕክምና ርዳታ እንዲያገኙ መደረጉን አስታውቋል፡፡
ስደተኞቹ የሚገኙበት የመተማ ወረዳ አስተዳደሪ አቶ ደሳለኝ ሞገስ በበኩላቸው፣ ከመጠለያዎች ወጥተው በመንገድ ዳር እየኖሩ ያሉት ስደተኞች፥ “ወደተዘጋጀላቸው ዐዲሱ የአፍጥጥ ካምፕ እንዲገቡ እያወያየናቸው ነው፤ ካልኾነ ግን የፌደራሉ መንግሥት እንዲያነሣቸው ሪፖርት እናደርጋለን፤” ብለዋል፡፡ስደተኞቹ ግን ፍላጎታቸው ከኢትዮጵያ መውጣት መኾኑን ገልጸዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ይከታተሉ፡፡
መድረክ / ፎረም