በደቡብ ምስራቃዊ የአሜሪካ ግዛቶች ለህይወት አስጊ ሁኔታ በፈጠረው ከባድ ዝናባማ ማዕበል "ሀሪኬን ዴቢ" ምክንያት ፍሎሪዳ ጆርጂያ እና ደቡብ ካሮላይና አስቸኳይ ጊዜ ታውጇል።
ዴቢ ሰሜናዊ ፍሎሪዳ ውስጥ ትላንት ሰኞ ጋብ ቢልም አደገኛነቱ የቀጠለ ሲሆን ቢያንስ አራት ሰዎች እንደገደለ ተዘግቧል።
ብሔራዊ የሀሪኬን ክትትል ማዕከል ትላንት ሰኞ ከቀትር በኋላ ባወጣው ማስጠንቀቂያ ነዋሪዎች ራሳቸውን እና ንብረታቸውን ከፍታው እያየለ ከሚሄደው ጎርፍ እንዲጠብቁ አሳስቧል።
የፍሎሪዳ አገረ ገዢ ሮን ደ ሳንቲስ 3000 የብሔራዊ ጦር ተጠባባቂ ኅይሎችን ለእርዳታ ሥራ አንቀሳቅሰዋል።
የአየር ሁኔታ ትንበያ ባለሞያዎች ከባድ ዝናባማው ማዕበል ፍሎሪዳ እና ሌሎችም የደቡብ ምስራቅ ዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ላይ እጅግ አውዳሚ ጎርፍ እንደሚያስከትል አስጠንቅቀዋል።
መድረክ / ፎረም