በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያ ፖሊሶች የሩሲያ ባንዲራ የያዙ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ማሰራቸውን ተናገሩ


በቀጠለው የናይጀርያ ተቃውሞ ሰልፈኞቹ የሩስያን ባንዲራ ይዘው ታይተዋል፣ ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. REUTERS/Stringer
በቀጠለው የናይጀርያ ተቃውሞ ሰልፈኞቹ የሩስያን ባንዲራ ይዘው ታይተዋል፣ ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. REUTERS/Stringer

የናይጄሪያ ፖሊሶች የሩሲያን ባንዲራዎች ያነገቡ ከ90 የሚበልጡ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ማሰራቸውን ዛሬ ማክሰኞ አስታውቀዋል።

እጅግ ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ላይ በምትገኘው ናይጄሪያ ባሳለፍነው ሳምንት በሺዎች የተቆጠሩ ሰዎች ሰልፍ ወጥተው በመንግሥቱ ፖሊሲዎችና በኑሮ ውድነቱ ላይ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

በአብዛኞቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር የተደረገውን ግጭት ተከትሎ የተቃውሞ እንቅስቃሴው በረድ ያለ ቢሆንም ካዱና እና ካኖን ጨምሮ በሰሜን ናይጄሪያ ግዛቶች ውስጥ ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ትላንት ሰኞ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።

አንዳንዶቹ ሰልፈኞች የሩሲያን ባንዲራ አንግበው በፈረንሳይ የዜና ወኪል ዘጋቢ በሌሎች የአይን እማኞች የታዩ ሲሆን የሩሲያ ኤምባሲ ግን በድረገጹ ባወጣው መግለጫ "በጉዳዩ እጃችን የለበትም" ብሏል።

ሰሜን ናይጄሪያ ከሳህል ግዛት አጎራባቾቿ ጋር ጠንካራ የባሕል ፥ የሐይማኖት፥ የማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር አላት። በተከታታይ መፈንቅለ መንግሥት በተካሂዱባቸው የናይጄሪያ ጎረቤት ሀገራት ያሉት ወታደራዊ መሪዎች በምዕራባዊያን የሀገሮቻቸው አጋሮች ላይ ፊታቸውን በማዞር ከሩስያ ጋር ሽርክናቸውን በማጠናከር ላይ እንዳሉ ይታወቃል።

በናይጄሪያ የተቃውሞ ሰልፍ በተጀመረበት ባለፈው ሐሙስ የጸጥታ ኃይሎች ቢያንስ 13 ሰዎችን እንደተገደሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አመልክቷል። ሰባት ሰዎች ሞተዋል ያለው ፖሊስ በበኩሉ በግድያው የለንበትም ሲል አስተባብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG