በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባንግላዴሽ ተቃዋሚዎች የኖቤል የሰላም ተሸላሚው መሐመድ ዩኑስ ሀገሪቱን እንዲመሩ እንደሚፈልጉ ተናገሩ


ፋይል፡ የኖቤል ተሸላሚው መሐመድ ዩኑስ ፣ የካቲት 24 ቀን 2016 ዓ.ም. (AP Photo/Mahmud Hossain Opu, File)
ፋይል፡ የኖቤል ተሸላሚው መሐመድ ዩኑስ ፣ የካቲት 24 ቀን 2016 ዓ.ም. (AP Photo/Mahmud Hossain Opu, File)

ለበርካታ ዓመታት የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን ሼክ ሃሲናን ከስልጣን ያስወገደው የተማሪዎች ተቃውሞ አደራጅ የኖቤል የሰላም ተሸላሚው መሐመድ ዩኑስ የሀገሪቱ የሽግግር መሪ እንዲሆኑ እንደሚፈልጉ ተናገሩ።

ሼክ ሃሲና ትላንት ሰኞ ስልጣናቸውን የለቀቁ ሲሆን የሀገሪቱ ፕሬዚደንት እና የጦር ኅይሉ አዛዥ በአፋጣኝ ጊዜያዊ መንግሥት እንደሚቋቋም ተናግረዋል።

የተማሪዎቹ ተቃውሞ አደራጅ ናሂድ ኢስላም ዛሬ ማክሰኞ በማሕበራዊ መገናኛ ባወጣው ጽሁፍ " የተቃውሞው መሪዎች ዩኑስን አነጋግረዋቸዋል፥ አመራሩን ለመረከብ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸውልናል" ብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG