በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ ሄዝቦላን ዒላማ ባደረገ የአየር ጥቃት አራት ሰው መግደሏ ተገለጸ


ይህ ከሰሜን እስራኤል የተወሰደው ምስል እስራኤላውያን በደቡብ ሊባኖስ ድንበር ኪያም መንደር ላይ ባደረሱት የቦምብ ጥቃት የተፈጠረውን ጢስ ያሳያል፣ ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም.
ይህ ከሰሜን እስራኤል የተወሰደው ምስል እስራኤላውያን በደቡብ ሊባኖስ ድንበር ኪያም መንደር ላይ ባደረሱት የቦምብ ጥቃት የተፈጠረውን ጢስ ያሳያል፣ ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም.

የእስራኤል ኃይሎች ዛሬ ማክሰኞ ደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ የአየር ጥቃት አድርሰው አራት ሰዎች መግደላቸውን የሊባኖስ የጤና ባለስልጣናት ተናገሩ።

የእስራኤል የጦር ኃይል ናባቲዬ የተባለው አካባቢ ላይ ያደረሰው ጥቃት የሄዝቦላ ታጣቂዎችን ዒላማ ያደረገ መሆኑን የተናገረ ሲሆን ሄዝቦላ በበኩሉ እስራኤል ላይ ያነጣጠረ የድሮን ጥቃት አድርሰናል ሲል ዛሬ አስታውቋል።

ጋዛ ሰርጥ ላይ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የሚካሄደውን ጦርነት ተከትሎ በሁለቱ ወገኖች መካከል ድንበር ተሻጋሪ ግጭቱ እየተባባሰ የሄደ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በአካባቢው እንዳይስፋፋ ለመከላከል ጥረት እያደረገ ነው።

ባለፈው ሳምንት እስራኤል ቤይሩት ውስጥ የሄዝቦላ ታጣቂዎች አዛዡን መግደሏን እና የሃማሱ የፖለቲካ መሪ ቴህራን ውስጥ መገደላቸውን ተከትሎ ስጋቱ እየተባባሰ ሄዷል። ኢራን እና ሃማስ እስራኤልን የሃማሱን መሪ በመግደል ወንጅለዋታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ደቡብ ኮሪያ ዜጎቿ በአስቸኳይ ከሌባኖስ እና ከእስራኤል እንዲወጡ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ያወጡ ሀገሮችን ዛሬ ተቀላቅላለች ።

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን እና የእስራኤል የመከላከያ ሚንስትር ዮአቭ ጋላንት ትላንት ሰኞ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ የተነጋገሩ ሲሆን ኦስተን " ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን እና ሄዝቦላን ከመሳሰሉ ተባባሪዎቿ ጥቃት ለተጋረጠባት ለእስራኤል ጸጥታ ያላትን የማያወላውል ቁርጠኛ ድጋፍ" እንዳረጋገጡላቸው ከፔንታጎን የወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ትላንት ሰኞ የኢራን ተባባሪ ታጣቂ ቡድን ምዕራባዊ ኢራቅ ውስጥ በዩናይትድ ስቴትስ ኅይሎች ላይ ያደረሰው ጥቃት ኢራን የአካባቢውን ጸጥታ በአደገኛ ደረጃ ለማደፍረስ መነሳቷን የሚያሳይ እንደሆነ ሚንስትሮቹ እንደተስማሙበት የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አመልክተዋል።

በጥቃቱ በርካታ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ አባላት መቁሰላቸውን አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ባለስልጣን ለቪኦኤ ገልጸዋል

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG