በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካማላ ሃሪስ  የሚኒሶታ አገረ ገዢ ቲም ዎልዝን ለእጩ ምክትል ፕሬዚደንትነት  መረጡ


ፋይል - የሚኒሶታ ገዥ ቲም ዎልዝ በሴንት ፖል ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሲሰጡ፣ ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም.
ፋይል - የሚኒሶታ ገዥ ቲም ዎልዝ በሴንት ፖል ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሲሰጡ፣ ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም.

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ካማላ ሃሪስ የሚኔሶታ አገረ ገዢ ቲም ዎልዝን እጩ ምክትል ፕሬዚደንታቸው እንዲሆኑ መርጠዋቸዋል።

ምክትል ፕሬዚደንት ሀሪስ ቲም ዎልዝን መምረጣቸውን ዛሬ ማክሰኞ ይፋ ያደረጉት በፔንሲልቬኒያ ግዛት ፊላዴልፊያ ከተማ ከሚካሄደው የዲሞክራቲክ ፓርቲው እጩ ተፎካካሪዎች የምርጫ ዘመቻ አስቀድመው ነው።

ሃሪስ ለደጋፊዎቻቸው በቴሌፎን የጽሁፍ መልዕክት ባስተላለፉት ቃል " የሚኒሶታ አገረ ገዢ ቲም ዎልዝ በምክትል ፕሬዚደንታዊ እጩነት አብረውኝ በፕሬዚደንታዊ ምርጫ ዘመቻው እንዲወዳደሩ መወሰኔን ሳስታውቅ በደስታ ነው" ብለዋል።

ሀሪስ አስከትለውም "ቲም ለሚኔሶታ ቤተሰቦች በመሥራት ታላላቅ ክንዋኔዎችን ያስመዘገቡ በትግል የተፈተኑ መሪ ናቸው" ብለው "ወደምርጫ ዘመቻችን እንዲሁም ወደምክትል ፕሬዚደንት ጽሕፈት ቤት ይህንኑ በመርሕ ላይ የተመሠረተ አመራር ይዘው እንደሚመጡ አውቃለሁ" ብለዋል።

ሃሪስ ከፊላዴፊያ በማስከተል በፕሬዚደንታዊ ምርጫው ማን እንደሚያሸንፍ የሚወስን ቁልፍ ሚና ያላቸው በሆኑት ዊስከንሲን፥ ሚሺጋን፥ አሪዞና እና ሰሜን ካሮላይና በዚህ ሳምንት የምርጫ ዘመቻዎች ያካሂዳሉ።

ዶናልድ ትረምፕ ጄ ዲ ቫንስን እጩ ምክትል ፕሬዚደንታቸው አድርገው በቅርቡ በተካሄደው በሪፐብሊካን ፓርቲው ጉባኤ ላይ መሰየማቸው ይታወሳል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG