በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ አንድ ቤት ውስጥ የታጎሩ 90 ኢትዮጵያውያን ፍልስተኞች አዳነ


የደቡብ አፍሪካ ካርታ
የደቡብ አፍሪካ ካርታ

ጆሃንስበርግ ውስጥ በሚገኝ አንድ ይዞታ ያለፍላጎታቸው ተይዘው የታጎሩ 90 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን ማዳኑን የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ዛሬ አስታወቀ።

ኢትዮጵያውያኑ የተገኙት ፍልስተኞችን አፍኖ ወደ ይዞታው የሚወስድ ግለሰብ መኖሩ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ሲያፈላግ ከቆየ በኋላ መሆኑን ፖሊስ ዛሬ ሰኞ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በአፈና እና በህገወጥ የሰዎች ዝውውር የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውና በፍርድ ቤት ክስ እንደሚመስረትባቸው ፖሊስ አክሎ ገልጿል፡፡

በህገ ወጥ መንገድ የተዘዋወሩት ኢትዮጵያውያኑ ፍልስተኞች የታሰሩት በአደገኛ ሁኔታ ትንሽ ክፍል ውስጥ ታጉረው እንደነበር ፖሊስ አመልክቷል፡፡

ፍልስተኞቹ ለህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውም ተነግሯል፡፡

ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማድረስ በተለያዩ የደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት የሚደረገው ህገ-ወጥ ዝውውር ኢንተርፖልን ጨምሮ ባለስልጣናትን አሳስቧል።

እ.ኤ.አ. በ2020 ሞዛምቢክ ውስጥ ከኢትዮጵያ የመጡ ቢያንስ 64 ሰዎች እቃ መጫኛ ውስጥ ሞተው ተገኝተዋል። እ ኤ አ በ2022 ዓም እንዲሁ የ30 ኢትዮጵያውያን ፍልስተኞች አስከሬን በማላዊ የጅምላ መቃብር ውስጥ ተገኝቷል። በዚያው ዓመት የ27 ኢትዮጵያውያን አስከሬን ዛምቢያ ውስጥ ተጥሎ መገኘቱም መዘገቡ ይታወሳል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG