በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረትና ደህንነት ዙርያ እየመከሩ ነው 


ፋይል፡ በሚያዝያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. በዋይት ሀውስ በቀረበው በዚህ ምስል፣ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ከብሄራዊ የደህንነት ቡድናቸው አባላት ጋር ሲመክሩ ያሳያል፣ (Adam Schultz/The White House via AP)
ፋይል፡ በሚያዝያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. በዋይት ሀውስ በቀረበው በዚህ ምስል፣ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ከብሄራዊ የደህንነት ቡድናቸው አባላት ጋር ሲመክሩ ያሳያል፣ (Adam Schultz/The White House via AP)

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዛሬ ሰኞ በመካከላለኛው ምስራቅ ስላለው ውጥረት ከብሄራዊ የደህንነት አማካሪያቸው ጋር እየተወያዩ ሲሆን ከዩርዳኖሱ ንጉሥ ዳግማዊ አብዱላህ ጋር በስልክ ይገናኛሉ፡፡

ውይይቱ የሚካሄደው የእስራኤል መሪዎች በኢራን ወይም በወኪሎችዋ ጥቃት ቢሰነዘርባቸው አጸፋው ተመጣጣኝ የሆነ "ከባድ ዋጋ" እንደሚያስከፍል ባስጠነቁቀበት ወቅት ነው፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛሬ በሰጡት መግለጫቸው ኢራን "በቀጣናው ያለውን ውጥረት ለማባባስ እንደማትፈልግ" ነገር ግን ባለፈው ሳምንት ቴህራን ውስጥ የሃማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሃኒዬን የገደለውን ጥቃት ተከትሎ እስራኤልን የመቅጣት መብት አላት ብለዋል።

ኢራን የሃማስ መሪ ሃኒዬ ግድያ የተፈጸመው እስራኤል በኢራን የሚደገፈውን የሂዝቦላ ጦር አዛዥ በቤይሩት የተገደለበትን የአየር ጥቃት ከፈጸመች ሰዓታት በኋላ በመሆኑ እስራኤልን ተጠያቂ አድርጋለች፡፡

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ኢራን እና ወኪሎቿ እስራኤልን “በሽብር አንቆ” ለመክበብ እየፈለጉ ነው ሲሉ ትላንት እሁድ ተናግረዋል፡፡

“በየትኛውም ግንባር በየትኛውም መድረክ በቅርበትም ሆነ በርቀት እነሱን ለመጋፈጥ ቆርጠን ተነስተናል” ያሉት ኔታኒያሁ “እኛን ሊጎዳን የሚፈልግ ማንኛውም ወገን በጣም ከባድ ዋጋ ይከፍላል” ብለዋል፡፡

ዛሬ ሰኞ፣ ቱርክ እና ጃፓን፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ፈረንሳይ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝና ዮርዳኖስን በመቀላቀል ሊከተል የሚችለውን አደጋ በማስጠንቀቅ ዜጎቻቸው ሊባኖስን ለቀው እንዲወጡ መክረዋል፡፡

ትላንት እሁድ ኢራን የነበሩት የሊባኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አይማን ሳፋዲ በአካባቢው ሰላም፣ ደህንነት እና መረጋጋት እንዲሰፍን ሁኔታውን ማባባስ እንዲቆም ኢራንን አሳስበዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ትላንት እሁድ ከእስራኤሉ አቻቸው ዮአቭ ጋላንት ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሎይድ አሜሪካ ለእስራኤል ደህንነት ጠንካራ ድጋፍ እንደምትሰጥ በማረጋገጥ ከኢራን እና መሠረቱን ሊባኖስ ካደረገው ሂዝቦላ እንዲሁም የየመኑ ሁቲ ከመሳሰሉት የኢራን ወኪሎች የሚሰንዘርባትን ጥቃት ለመመከት እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት አላት ብለዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ የጦር ተዋጊ ጀት ተሸካሚዎችን ተጨማሪ የአየር መሣሪዮችን ወደ አካባቢው ማንቀሳቀሷን የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ፔንታጎን ባለፈው ዓርብ አስታውቋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንም የመካከለኛው ምስራቅን ውጥረት ስለ ማረጋጋት አስፈላጊነት ትላንት እሁድ ከቡድን 7 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG