በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን የሩሲያ ኢላማዎችን ዘልቃ በመግባት መምታት ጀመረች


የዩክሬን አየር ሃይል የታጠቃቸው ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች እና ሚሳዬል ነሐሴ 4 ቀን 2024።
የዩክሬን አየር ሃይል የታጠቃቸው ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች እና ሚሳዬል ነሐሴ 4 ቀን 2024።

ዩክሬን የረዥም ርቀት ጥቃቷን በማጠናከር ባላፉት 24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ የሩሲያን ባህር ሰርጓጅ መርከብ ስታሰጥም የአውሮፕላን ማረፊያዎችን መደብደቧን አስታውቃለች፡፡

የሩሲያ ባለሥልጣናትም የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች አንድ የመኖሪያ አፓርትመንት ህንጻ በመምታታቸው የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ተናግረዋል፡፡

ዩክሬን ከሀምሌ ወር ጀምሮ ሩሲያን ለመምታት የረዥም ርቀት ሚሳዬሎችን መጠቀም እንድትችል አጋሮቿን በመጠየቅ ጫና ብታደርግም ምዕራባውያን በተለይም አሜሪካ በሞስኮ በኩል ሁኔታው ሊባባስ ይችላል በሚል ስጋት ተቃውመዋል፡፡

ዩክሬን በሩሲያ ቁጥጥር ስር ወደ ምትገኘው ክሬሚያ ዘልቆ በመግባት “ኪሎ ክላስ” የሚባል በናፍጣና ኤሌክትሪክ የሚሰራ ባህር ሰርጓጅ መርከብ እና S-400 የተባሉ የሩሲያ አየር መቃወሚያ ሚሳዬሎችን መምታቷን አስታውቃለች፡፡

የአየር መቃወሚያ መሣሪያው የሩሲያ ጦር የሎጀስቲክስና ትራንስፖርት መናኻሪያ የሆነውን ወሳኙን የኬርች ሰርጥ ድልድይ የሚጠብቅ እንደነበር የዩክሬን መከላከያ ትላንት ቅዳሜ ያወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ሩሲያ ባለፈው ወር የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠሩ የረዥም ርቀት ጥቃቶችን አካሂዳለች፡፡

ተንታኞች የሩሲያን ጦር አቅም ለማዋረድ ዩክሬንን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG