በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የውጭ ዜጎች ሊባኖስን ለቀው እንዲወጡ ተነገራቸው


የሃማስ እና ሂዝቦላ መሪዎች መገደላቸውን በማውገዝ ሊባኖስ ውስጥ አደባባይ የወጡ ደጋፊዎች እኤአ ነሀሴ 2 2024 (ፎቶ ሮይተርስ)
የሃማስ እና ሂዝቦላ መሪዎች መገደላቸውን በማውገዝ ሊባኖስ ውስጥ አደባባይ የወጡ ደጋፊዎች እኤአ ነሀሴ 2 2024 (ፎቶ ሮይተርስ)

የጦርነት ስጋት እየጨመረ በመምጣቱ የውጭ ዜጎች ሊባኖስን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ የሚሰጠው ማሳሰቢያ ጨምሯል፡፡

ፈረንሣይ ዛሬ እሁድ ኢራን እና አጋሮችዋ ከፍተኛ የሂዝቦላና ሃማስ ኃላፊዎች የተገደሉበትና እስራኤልን ጥፋተኛ ላደረጉበት ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ እንደሆኑ ማሳወቃቸውን ተከትሎ “ሁኔታው እጅግ አደገኛ ነው” ስትል አስጠንቅቃለች፡፡

"በጣም አደገኛና ተለዋዋጭ በሆነ የደህንነት ሁኔታ ውስጥ" የፈረንሳይ ዜጎች ወደ ሊባኖስ ከመጓዝ እንዲቆጠቡ እና በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትም በተቻለ ፍጥነት አሁኑን በአስቸኳይ ለመውጣት እንዲዘጋጁ" ሲል በፓሪስ የሚገኘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ እና ብሪታኒያም ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያዎች ሰጥተዋል፡፡

በርካታ ምዕራባውያን ሀገሮች ወደ አካባቢው የሚያደርጓቸውን በረራዎች ሰርዘዋል፡፡

የካታር አየር መንገድም ከዛሬ እሁድ አንስቶ ቢያንስ እስከ ሰኞ ድረስ ከሊባኖስ በዶሃ ቤይሩት በኩል የሚደረጉ በረራዎች በቀኑ ክፍለጊዜ ብቻ እንዲደረጉ በማዘዝ የምሽት በረራዎችን አቋርጧል፡፡

የጋዛ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ ከእስራኤል ጦር ጋር በየቀኑ ሊባል የሚችል የተኩስ ልውውጥ የሚያደርገው፣ በኢራን የሚደገፈው የሊባኖሱ ሂዝቦላህ፣ ተዋጊዎቹ በአንድ ሌሊት ወደ እስራኤል ሰሜናዊ ክፍል ሮኬቶች መተኮሳቸውን አስታውቋል።

የእስራኤል ጦር ከሊባኖስ ወደ 30 የሚጠጉ ሮኬቶች የተወነጨፉ ሲሆን አብዛኞቹ ተጠልፈዋል ብሏል።

አሜሪካ የጦር መርከቦችን እና ተዋጊ ጄቶችን በማንቀሳቀስ ሰራተኞቿን ለመጠበቅ እና እስራኤልን ለመከላከል እየሰራች ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ጦር በጋዛ የሚያካሂደውን ጥቃት የቀጠለ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ወደ 50 የሚጠጉ የሽብር ኢላማዎችን መምታቱን አስታውቋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG