በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ጦሯን ለማጠናከር ተጨማሪ ወታደራዊ ሃይል መላኳን አስታወቀች 


በአሜሪካ የባህር ኃይል በተለቀቀው በዚህ ፎቶግራፍ ላይ የኒሚትዝ ክፍል አውሮፕላን ተሸካሚ ዩኤስ ኤስ ቴዎዶር ሩዝቬልት የጦር መርከብን ያሳያል;
በአሜሪካ የባህር ኃይል በተለቀቀው በዚህ ፎቶግራፍ ላይ የኒሚትዝ ክፍል አውሮፕላን ተሸካሚ ዩኤስ ኤስ ቴዎዶር ሩዝቬልት የጦር መርከብን ያሳያል;

አሜሪካ እስራኤልን ለመደገፍ በመካከለኛው ምስራቅ እና አካባቢው የተሰማራውን መከላከያዋን ለማጠናከር የጦር መርከቦች እና ተዋጊ ጄቶችን መላኳን አስታውቃለች፡፡ ይህም ከኢራን ሊሰንዘር የሚችል ወታደራዊ ጥቃትን በመስጋት ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን ትላንት ተጨማሪ ሃብትና አቅም ወደ መካከለኛው ምስራቅና አንዳንድ የአውሮፓ አካባቢዎች እንዲላክ ትዕዛዝ ፈርመዋል፡፡

ይህ የአሜሪካ ውሳኔ የታወቀው ቴህራንና አጋሮቿ በሂዝቦላ ወታደራዊ አዛዥና የሃማስ የፖለቲካ መሪ ግድያን ተከትሎ የበቀል ርምጃ እንደሚወስዱ መዛታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ከላከቻቸው መካከል “ዩ ኤስ ኤስ አብርሃም ሊንከን የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ የጦር መርከብን ትገኝበታለች፡፡ አብረውም የባላስቲክ ሚሳኤልን ማውደም የሚችሉ መሳሪያዎችና የጦር መርከበኞች ወደ ስፍራው ማቅናታቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህ ሌላም ተጨማሪ ተዋጊ ቡድን ወደ አካባቢው እየላከች ሲሆን በመሬት ላይ የተመሰረተ የሚሳኤል መከላከያ አቅምን ለማሰማራት እርምጃዎችን እየወሰደች ነው።

ፔንታጎን ተጨማሪ የተላኩት የጦር መርከቦችና አውሮፕላኖች መቼ እንደሚደርሱ ባይገልጽም ትላንት አርብ ባወጣው መግለጫ በኢራንና አጋሮቿ ሊኖር የሚችለውን ቀጠናዊ የውጥረት መባባስን ለመግታት ርምጃው አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል

ይህ ውሳኔም የመከላከያ ሚንስትሩ ሎይድ ኦስቲን ከእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ለእስራኤል ተጨማሪ ድጋፍ ለመስጠት ቃል ከገቡ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ይፋ ስለመደረጉም ተገልጿል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG