በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፈረንሳይ የምዕራባዊ ሰሃራ ነጻነትን በሚመለከት የአቋም ለውጥ አደረገች 


ፋይል - የፖሊሳሪዮ ግንባርን 50ኛ አመት በአውሴሬድ ካምፕ፣ አልጄሪያ፣ ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በተከበረበት ወቅት ወታደራዊ ሰላምታ ሲሰጥ ያሳያል
ፋይል - የፖሊሳሪዮ ግንባርን 50ኛ አመት በአውሴሬድ ካምፕ፣ አልጄሪያ፣ ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በተከበረበት ወቅት ወታደራዊ ሰላምታ ሲሰጥ ያሳያል

ፈረንሳይ አዋዛጋቢውን የምዕራባዊ ስሃራ ነጻነትን በተመለከተ የሞሮኮን እቅድ እንደምትደግፍ አስታውቃለች፡፡

ይህም ከአስርት አመታት በላይ ይዛው የቆየችውን አቋሟን የቀየረ ሲሆን ራሷንም በቆመው የተባበሩት መንግስታ ድርጅት የሰላም ሂደት ውስጥ እየጨመረ ከመጣው ሞሮኮን ከሚደግፉ ሃገራት ዝርዝር ውስጥ አካታለች፡፡

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለንጉሥ መሐመድ ስድስተኛ በፃፉት ደብዳቤ ላይ ሞሮኮ እ.ኤ.አ. በ 2007 ለክልሉ ሉዓላዊነት የተገደበ የራስ ገዝ አስተዳደር እንዲኖር ያቀረበችው እቅድ ግጭቱን ለመፍታት "ብቸኛ መሰረት" ነው ማለታቸው ተገልጿል።

ይህ የፈረንሳይ የአቋም ለውጥም ላለፉት አስርት አመታት የሳህራዊ ተወላጆች ህጋዊ ተወካይ እንደሆነ ለሚገልጸው የግዛቷ የነጻነት አቀንቃኝ የፖሊሳሪዮ ግንባርን እንደሚጎዳ ተነግሯል፡፡

የማክሮን ርምጃ የግዛቱን ውዝግብ ቁልፍ መርሆች የሚለውጥ ባይሆንም ፈረንሳይ ከሞሮኮ ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ሊያጠናክረው እንደሚችል ግን ተገልጿል፡፡

የሞሮኮው ንጉስ መሀመድ ስድስተኛ ንጉሣዊ ካቢኔ ባወጣው መግለጫ የፈረንሳይን የአቋም ለውጥን "ትልቅ እድገት" ሲል አድንቋል፡፡

ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ከእስራኤል፣ ከስፔን እና በግዛቱ ውስጥ ቆንስላ መሥሪያ ቤቶችን ያቋቋሙ የአፍሪካ ሃገራትም ተመሳሳይ ለውጦችን ይከተላሉ ተብሎ ተጠብቋል።

ምዕራባዊ ሰሃራ የኮሎራዶን ያህል ስፋት ያላት ስትሆን በፎስፌትስ ከበለፀገው በረሃማ ስፍራ አካባቢ እስከ በአሳ የበለፀገ በአትላንቲክ የባህር ዳርቻ ድረስ የተዘረጋች ናት።

የቀድሞ የስፔን ቅኝ ግዛት የነበረችውን ምዕራባዊ ስሃራን እ አ አ በ1975 ሞሮኮ የግዛቷ አካል አድርጋ የያዘች ሲሆን ይህን ተከትሎም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት "ራስን የማያስተዳድር ግዛት” ተድርጎ ከሚቆጠረው የነጻነት አቀንቃኝ የፖሊሳሪዮ ግንባር ጋር ግጭት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸው መቆየቱ ተገልጿል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG