የሂዝቦላህ መሪ ሀሳን ናስርላህ ታጣቂ ቡድኑ ከእስራኤል ጋር ያለው ግጭት ወደ “አዲስ ምዕራፍ” ገብቷል ሲሉ አስጠነቀቁ።
ናስረላህ ይህን የተናገሩት በዚህ ሳምንት ቤዪሩት እና ቴህራን ውስጥ የሂዝቦላ አዛዥ እና የሃማስ ፖለቲካ መሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ናስረላህ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት እስራኤል ቤይሩት ላይ ባደረገችው ጥቃት ለተገደለው ለአዛዡ ፉአድ ሽኩር በተፈጸመ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ነው፡፡
እስራኤል በቤሩት የሂዝቦላህ አዛዥ ፉአድ ሽኩርን እና ሌሎችን የገደለውን ጥቃት መፈፀሟን አረጋግጣለች።
እስራኤል በቁጥጥሯ ስር በሚገኘው ጎላን ሃይትስ 12 ህጻናትን ከተገደሉበት የሮኬት ጥቃት ጀርባ የሽኩር እጅ አለበት ብትልም ሂዝቦላ የእስራኤልን ክስ አስተባብሏል።
የሂዝቦላህ መሪ ናስራላህ "በጣም የተጠና የበቀል እርምጃ" እንደሚወሰድ ፍንጭ ቢሰጡም ዝርዝሩን አልገለጹም፡፡
የጋዛ ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሂዝቦላህ እና እስራኤል በየቀኑ ሊባል የሚችል የተኩስ ልውውጥ ቢያደርጉም እስካሁን ወደ ሙሉ ጦርነትን አልገቡም፡፡
ሊባኖስ እ.ኤ.አ. በ2006 ከእስራኤል ጋር ያካሄደችው ጦርነት እንዳይደግም በሚል ሂዝቦላ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ገብቷል።
ዓለም አቀፍ ባለስልጣናት የበቀል አዙሪቱ ወደ ከፍተኛ ጦርነት እንዳያመራ እየሰሩ ነው።
መድረክ / ፎረም